Thursday, August 11, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፓርትየደቡብ ክለቦች በኦሊምፒክ ሳምንት

  የደቡብ ክለቦች በኦሊምፒክ ሳምንት

  ቀን:

  የኦሊምፒክ ሳምንት ከሰኔ 16 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያ በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች እንደሚከበር ይጠበቃል፡፡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መርሐ ግብሩን አስመልክቶ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች አመራሮች ጋር በመነጋገር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ በደቡብ ክለቦች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመሆን መፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከክልሉ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር የመፍትሔው አካል ለመሆን ጥረት እያደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡

  ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ በርካታ ተጫዋቾችን በማፍራት የሚታወቀው የደቡብ ክልል አሁን ላይ ክለቦቹ እግር ኳሳዊ ባልሆኑ ምክንያቶች አንዱ ሌላውን የሚመለከትበት ዕይታ የተዛባ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ይህም የክልሉ ክለቦች እርስ በርሳቸው ብቻ ሳይሆን ከአጎራባች ክልሎች ከሚመጡ ቡድኖች ጭምር የሜዳ ተጠቃሚነታቸውን ዕድል አሳልፈው እንዲሰጡ ምክንያት ሆኗል፡፡

  ባለፈው የውድድር ዓመት ይህ አሁን በደቡብ ክልል የሚስተዋለው ችግር በአማራና በትግራይ ክልሎች ክለቦች መካከል ተከስቶ የነበረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት የሁለቱም የክልል አመራሮችም ሆኑ ክለቦቹ ወደ ትክክለኛው መስመር ገብተው ክለቦቻቸው እግር ኳሳዊ መርሕን ተከትለው በየሜዳቸው እንዲጫወቱ በመደረጉ ያስገኘላቸው ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፋይዳ ትልቅ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡

  በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከሚሳተፉ 16 ቡድኖች መካከል አራቱ ማለትም ሐዋሳ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና፣ ወላይታ ድቻና ደቡብ ፖሊስ የክልሉ ክለቦች ሲሆኑ፣ የ22ኛ ሳምንት የጨዋታ መርሐ ግብር በሜዳቸው ማድረግ የነበረባቸው የደቡብ ፖሊስና የወላይታ ድቻ እንዲሁም የሐዋሳ ከተማ ቡድኖች በችግሩ ምክንያት ከሜዳቸው ውጪ በገለልተኛ ሜዳ እንዲጫወቱ ተደርጓል፡፡

  የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በክልሉ መዲና ሐዋሳ ከተማ ላይ የኦሊምፒክ ሳምንት ፕሮግራም እንደሚያከናውን አስታውቋል፡፡ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈዴሬሽን አመራሮች ጋር በመሆን ርዕሰ መስተዳድሩን አቶ ሚሊዮን ማቲዮስና ሌሎች የክልሉ አመራሮችን በማግኘት በክልሉ ክለቦች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ተፈቶ ወደ ነበረበት በሚመለስበት ጉዳይ ላይ መነጋገራቸው ታውቋል፡፡

  አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ በክልሉ ክለቦች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ተቀባይነት እንደሌለው፣ ክለቦቹ ቀድሞ ወደ ነበሩበት የውድድር ሥርዓት እንዲመለሱ እንደሚደረግ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡ ይህንኑ ለኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር) እና ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ቃል እንደገቡላቸው ታውቋል፡፡

  ከሰኔ 16 ጀምሮ የሚከበረውን የኦሊምፒክ ሳምንት አስመልክቶ ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ‹‹ክልላቸው የኦሊምፒዝምን ፍልስፍና መነሻ በማድረግ የሚከበረውን የኦሊምፒክ ሳምንት የሚያከናውነው፣ ስፖርት በሕዝቦች መካከል መቀራረብንና አንድነትን ከመፍጠር አኳያ ያለውን ፋይዳ በመረዳት ነው፣›› ማለታቸው ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የላከው ጋዜጣዊ መግለጫ ያስረዳል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት ጀመረ

  ሦስተኛ ዙር ሙሌት በዛሬው ዕለት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ...

  የክላስተር አደረጃጀት ፖለቲካዊ ውዝግብ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይባል የነበረውን አደረጃጀት...

  በወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው ከፍተኛ ሀብት ጥቅም ላይ እየዋለ አይደለም ተባለ

  በኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበው የተቀማጭ ገንዘብ መጠን...