Sunday, August 14, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -

  ታይገር

  ቀን:

  ታይገር እስያዊ እንስሳ ነው፡፡ በአፍሪካ ጨርሶ አይገኝም፡፡ ቀድሞ የሚገኝባቸው ሥፍራዎች፣ ከቱርክ ጀምሮ እስከ መካከለኛውና ምዕራብ እስያ ይደርስ ነበር፡፡ አሁን የሚገኝባቸው ግን፣ ከሕንድ እስከ ቪየትናም፣ ከዚያም በሳይቤሪያ፣ በቻይና፣ በኮሪያና በሱማትራ ኢንዶኔዥያ ነው፡፡ ከሁሉ የሚበልጠው ዓይነት ትልቁ ታይገር የሚገኘው በመስኮብ፣ በቻይናና በሰሜን ኮርያ ነው፡፡ የወንዱ ክብደት እስከ 306 ኪ.ግ ይደርሳል፡፡ የሴቷ ደግሞ እስከ 167 ኪ.ግ ይደርሳል፡፡

  ታይገሮች ከሌሎች ትላልቅ የድመት አስተኔ አባላት የሚለዩበት አንድ ባሕርይ፣ ውኃ መውደዳቸው ነው፡፡ ጥሩ ዋናተኞች ከመሆናቸው የተነሳ፣ በኪሎ ሜትሮች የሚቆጠር ስፋት ያላቸውን ጅረቶች ማቋረጥ ይችላሉ፡፡ እጅግ ሞቃት በሆነ ወቅትም በሐይቆችና ኩሬዎች ውስጥ በከፊል ሰጥመው ይንጋለላሉ፡፡ አንዳንዴም ሰዎችን ከጀልባ ላይ ጠልፈው እንደሚደፍቁ ይታወቃል፡፡ አዞ ሳይቀር ገድለው በመብላት ይታወቃሉ፡፡

  ታይገሮች የሚያድኑት ከምሽት እስከ ንጋት ቢሆንም፣ ካመቻቸው በቀንም ያድናሉ፡፡ አድነው የሚበሉት አዞና ሰው ብቻ ሳይሆን፣ ርኤም፣ አሳማ፣ የዝሆንና የአውራሪስ ጥጃዎች፣ ጦጣዎች፣ ወፎች፣ ገበሎ አስተኔዎችና አሳም አይቀራቸውም፡፡

      ሰሎሞን ይርጋ (ዶ/ር) «አጥቢዎች» (2000)

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...