Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናሥጋት ባለባቸው አካባቢዎች ለሚሰጠው ብሔራዊ ፈተና የመከላከያ ሠራዊት ዕገዛ ተጠየቀ

  ሥጋት ባለባቸው አካባቢዎች ለሚሰጠው ብሔራዊ ፈተና የመከላከያ ሠራዊት ዕገዛ ተጠየቀ

  ቀን:

  በአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ እንደሚሰጥ የሚጠበቀው አገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና በሰላማዊ መንገድ እንዲከናወን፣ የመከላከያ ሠራዊቱ በተለይ የፀጥታ ሥጋት ባለባቸው አካባቢዎች ዕገዛ ሊያደርግ እንደሚገባ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ፡፡

  ቋሚ ኮሚቴው ሰኞ ግንቦት 12 ቀን 2011 .ም. ወቅታዊ አገር አቀፍ የፈተና ዝግጅቶችንና ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ፣ የትምህርት ሚኒስትሩን ጥላዬ ጌቴ (ዶ/ር) እና  የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርዓያ ብረ እግዚአብሔርን ጨምሮሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይቷል፡፡

  የፀጥታ ሥጋት ባለባቸው አካባቢዎች ለሚሰጠው አገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና ኤጀንሲው በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተነስቶ፣ በቋሚ ኮሚቴው አባላትና በሁለቱ ተቋማት ኃላፊዎች መካከል ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

  የሚኒስቴሩም ሆነ የኤጀንሲው ኃላፊዎች ከአካባቢ የፀጥታ አካላትና አመራሮች ጋር  በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ፈተናውን ለመስጠት የሚያዳግቱ አሥጊ ሁኔታዎች በዝርዝር ተተንትነው የተለዩ መሆኑን፣ ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ እስከ ወረዳ መዋቅር ድረስ የዘለቀ ሥራ እየተከናወነ እንደሆነም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

  ፈተናውሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ የምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነትናሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ሚኒስትሩ ጠይቀዋል፡፡

  ቋሚ ኮሚቴውም በቅንጅት አብሮ በመሥራት ዕገዛ እንደሚያደርግ ገልጾ፣ ሥጋት ባለባቸው አካባቢዎች የፀጥታ አስከባሪዎች ሕግ በማስከበር እንዲሳተፉና የመከላከያ ሠራዊቱ አስፈላጊውን ዕገዛ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

  ሰሞኑን በአንዳንድ አካባቢዎች የመምህራን አድማ ማድረግ ፈተናውን እንዳያስተጓጉለው ምን ሊሠራ ታስቧል የሚል ጥያቄ ከአንድ የቋሚ ኮሚቴ አባል ቀርቧል፡፡

  አድማው መምህራኑ የጠየቁት ጥያቄ ሙሉ ለሙሉ ባለመመለሱ የተከሰተ እንደሆነ ሚኒስትሩ ጠቁመው፣ በአድማው ምክንያት ፈተናው ችግር ላይ እንዳይወድቅ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በተጨማሪ፣ ከክልል አመራሮች ጋር በቅርበት እየተሠራ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

  በቅርቡ በሚሰጠው አገር አቀፍ ፈተና ኩረጃ የፀጥታ ሥጋት እንዳይሆን ኤጀንሲው በትኩረት መንቀሳቀስ እንዳለበት፣ የሰው ሀብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአጠቃላይ ትምህርት ንዑስ ሰብሳቢ / ራቢያ ኢሳ አሳስበዋል፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...