Sunday, August 14, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናምርጫ ቦርድ ለቀጣዩ ምርጫ ማስፈጸሚያ 3.7 ቢሊዮን ብር ጠየቀ

  ምርጫ ቦርድ ለቀጣዩ ምርጫ ማስፈጸሚያ 3.7 ቢሊዮን ብር ጠየቀ

  ቀን:

  በ2012 ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው ጠቅላላ ምርጫ ማስፈጸሚያ ይሆን ዘንድ የአራት ቢሊዮን ብር በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረበው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ከምክር ቤቱ የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር በተደረገ ውይይት ግብዓቶችን ወስዶ በጀቱን በመከለስ 3.7 ቢሊዮን ብር ለ2012 የምርጫ ማካሄጃ በጀት እንዲፈቀድለት ለምክር ቤቱ አቅርቦ እየተጠባበቀ እንደሆነ አስታወቀ፡፡

  ቦርዱ ይህን ያስታወቀው ሰኞ ግንቦት 19 ቀን 2011 ዓ.ም. በሳፋየር ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ሲሆን፣ መግለጫውን የሰጡት ደግሞ የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ናቸው፡፡

  ቦርዱ ያቀረበው ጥያቄ ባለፈው የምርጫ ወቅት ከነበረው በጀት  ከፍተኛ ጭማሪ ያለው ሲሆን፣ ይህም የሆነበት ዋነኛ ምክንያት የቀድሞዎቹን የምርጫ ኮሮጆዎች በግልጽ በሚያሳዩ ኮሮጆዎች ለመቀየርና በአንድ የምርጫ ጣቢያ አንድ የነበረውን የምርጫ ኮሮጆ ሁለት ለማድረግ በመታቀዱ፣ እያንዳንድ የድምፅ መስጫ ወረቀት የደኅንነት መለያ ቁጥርና የተወዳዳሪ ምሥልን የያዘ ሆኖ እንዲሠራ በመታቀዱ፣ የመራጮች ቁጥር በሕዝብ ቁጥር መሠረት በመሰላቱ፣ እንዲሁም ገለልተኛ ምርጫ አስፈጻሚዎችን ለመመልመልና ለማሠልጠን ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ እንደሆነ በመግለጫው ወቅት ተገልጿል፡፡

  የምርጫ በጀቱ ሲዘጋጅ የመራጮች ቁጥር 53.9 ሚሊዮን ይደርሳል ተብሎ መገመቱን ቦርዱ የገለጸ ሲሆን፣ ከዚህም መካከል 45.3 ሚሊዮን ሕዝብ ለመራጭነት ይመዘገባል ተብሎ እንደሚታሰብም አክሎ አስታውቋል፡፡

  በዚህም መሠረት በአንድ የምርጫ ጣቢያ በአማካይ 1,500 መራጮች ይመዘገባሉ የሚል ግምት የተወሰደ ሲሆን፣ በጀቱ 41,600 የምርጫ ጣቢያዎችን ታሳቢ በማድረግ መዘጋጀቱም ታውቋል፡፡

  ከዚህ ቀደም ቦርዱ የሚያስፈልገውን በጀት በገንዘብ ሚኒስቴር አማካይነት ያቀርብ እንደነበር ያስታወሱት ወ/ሪት ብርቱካን፣ ዘንድሮ ግን ቦርዱ ለመጀመርያ ጊዜ በጀቱን ለምክር ቤቱ በቀጥታ ማቅረቡን ገልጸው ይህም የገለልተኛ ተቋማት የበጀት ነፃነት መርህን መሠረት ያደረገ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

  ቦርዱ ለመጪው ምርጫ የሚያስፈልገውን በጀት አስመልክቶ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ስለሚኖር ትብብር የተወያየ መሆኑ ተጠቁሞ፣ በርካታ ደጋፊ አገሮች ድጋፍ ለማድረግ ውሳኔያቸውን ማስታወቃቸውን የቦርዱ ሰብሳቢ ገልጸዋል፡፡ በዚህም መሠረት በተለያዩ መስኮች የሚሰጠው ድጋፍ በግምት 900 ሚሊዮን ብር ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅም አክለው አብራርተዋል፡፡

  በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት ከበጀት ጉዳይ በተጨማሪ ቦርዱ እያከናወናቸው ስላሉ የሕግ ማዕቀፍ ማሻሻያዎች፣ ተቋማዊ ማሻሻያዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የውይይት መድረክ፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎች የሚደረግ ድጋፍ፣ ከሲቪክ ማኅበራት ጋር አብሮ መሥራት የሚቻልበትን ሁኔታ ስለማሻሻል፣ ከዓለም አቀፍ አገሮች ጋር ስለሚደረግ ትብብር፣ እንዲሁም በቀጣይ ውሳኔ ስለሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

  በዚህም መሠረት ቦርዱ የተሟላ አባላት ሲኖሩት ውሳኔ ለመስጠት በሒደት ላይ ያሉት ጉዳዮች የፓርቲዎች የዕውቅና  ጥያቄዎች፣ የድርጅታዊ መዋቅር ለውጥ፣ የምርጫ ዝግጅትና አፈጻጸም፣ እንዲሁም የሲዳማ ክልል ከመሆን ጥያቄ ጋር በተያያዘ የቀረበ የሕዝብ ውሳኔ ጥያቄ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

  ቦርዱ መጪው ምርጫ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት እንደሚከናወን፣ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ጊዜ መራዘም እንደማያስተጓጉለው ተገልጿል፡፡

  ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ተካሂዶ የነበረው አምስተኛው ጠቅላላ ምርጫ 319 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበት እንደነበር ይታወሳል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...