Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፓርትኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ በግብፁ የአፍሪካ ዋንጫ በቴክኒክ አባልነት እየተሳተፉ ነው

  ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ በግብፁ የአፍሪካ ዋንጫ በቴክኒክ አባልነት እየተሳተፉ ነው

  ቀን:

  ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማም ኢትዮጵያን ወክለዋል

  ለመጀመርያ ጊዜ 24 ቡድኖችን እያሳተፈ የሚገኘው 19ኛው የአፍሪካ ዋንጫ  ውድድር ዓርብ ሰኔ 14 ቀን 2011 ዓ.ም. በግብፅ መካሄድ ጀምሯል፡፡ በውድድሩም ኢትዮጵያ በኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማና በዋሊያዎቹ ዋና አሠልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ተወክላለች፡፡

  ኢንስትራክተር አብርሃም በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ የታደሙት፣ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ከጨዋታው አስቀድሞ አሥራ አምስት አባላትን ባካተተው የ2019ኙ የአፍሪካ ዋንጫ የቴክኒክ ጥናት ቡድን ውስጥ እንዲካተቱ ስለመረጣቸው ነው፡፡

  ኢንስትራክተር አብርሃምን ጨምሮ ለአፍሪካ አገሮች የብሔራዊ ቡድኖች ዋና አሠልጣኞች፣ የቴክኒክ ቡድኑን ቢቀላቀሉ ‹‹ይመጥናሉ አይመጥኑም›› የሚለውን መለየት የኦንላይን ፈተና ከወሰዱ ባለሙያዎች መካከል ብቁ ናቸው በማለት ስለመረጣቸው የዋሊያዎቹ ዋና አሠልጣኝ በግብፁ የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ እንደበቁ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

  ከሳምንት በፊት ወደ ግብፅ ያቀኑት ኢንስትራክተር አብርሃም፣ በአሁኑ ወቅት በምድብ ሁለት የሚገኙትን ብሔራዊ ቡድኖች ማለትም የናይጄሪያ፣ የጊኒ፣ የብሩንዲና የማዳጋስካር ቡድኖች ውድድራቸውን በሚያደርጉባትና ሁለተኛዋ ዋና ከተማ በሆነችው አሌክሳንድሪያ፣ ቡድኖቹ በውድድሩ ወቅት የሚኖራቸውን የቴክኒክ እንቅስቃሴ ከካፍ የቴክኒክ አማካሪ ከሚስተር ሚካኤል ቤንዜት ጋር በመሆን እየገመገሙ ይገኛሉ፡፡

  አሠልጣኝ አብርሃም በአፍሪካ ከሚገኙ የአሠልጣኞች አሠልጣኝ ተብለው በካፍ ከተመረጡ ጥቂት ኢንስትራክተሮች አንዱ ናቸው፡፡ አሠልጣኙ በአሌክሳንድሪያ የሚኖራቸው ቆይታም የምድብ ድልድሉ ማጣሪያ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚዘልቅ ሲሆን፣ በግማሽ ፍፃሜው ወቅትም ወደ ዋና ከተማዋ ካይሮ በማቅናት የግማሽ ፍፃሜውን ውድድሮች ቴክኒካዊ ብቃት መገምገም እንደሚቀጥሉ ታውቋል፡፡

  ካፍ በድረ ገጹ እንዳስታወቀው፣ የቡድኖቹን ቴክኒካዊ ብቃት የሚገመግሙት ኢንስትራክተሮች የየጨዋታውን ኮከብ ተጨዋቾች ምርጫ በማከናወን ለሽልማት የማጨት ሚናም ተሰጧቸዋል፡፡

  በዘንድሮ የአፍሪካ ዋንጫ 24 ቡድኖች በስድስት ምድቦች ተደልድለው የሚፎካከሩ ሲሆን፣ አዘጋጇ ግብፅ በምድብ አንድ ከዚምባቡዌ፣ ዴሞክራቲክ ኮንጎና ከምሥራቅ አፍሪካዊቷ ኡጋንዳ ጋር ተደልድላለች፡፡

  አወዳዳሪው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን፣ አዘጋጇ ግብፅ ከፍተኛ የሙቀት መጠን የሚታይበት የአየር ፀባይ ወቅት ላይ የምትገኝ በመሆኗ፣ ለተጫዋቾችና ለዳኞች፣ እንዲሁም በየጨዋታው ለሚሠማሩ ባለሙያዎች በቀዝቃዛ ውኃ የተነከሩ ፎጣዎችን ከማዘጋጀቱም ባሻገር፣ በየውድድሮቹ ወቅት እንደአስፈላጊነቱ ሁለት ጊዜ የጨዋታ ዕረፍት እንደሚደረግና ተጨዋቾችና ዳኞችም ከሙቀቱ ፋታ የሚሰበስቡበትን ጊዜ አመቻችቷል፡፡

  እ.ኤ.አ. በ1957 ሦስት አገሮች ማለትም በግብፅ፣ ኢትዮጵያና ሱዳን ሲሆኑ፣ የመጀመርያውን የአፍሪካ ዋንጫ በማንሳት በታሪክ የሠፈረችው ደግሞ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን የአፍሪካ ዋንጫ እያስተናገደች የምትገኘው ግብፅ ነበረች፡፡ ግብፅ የአፍሪካን ዋንጫ ሰባት ጊዜ በማንሳትም ቀዳሚ አገር መሆኗ ይታወቃል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...