Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፓርትለአፍሪካ ጨዋታዎች የተመረጡ አትሌቶች ያለመስፈርት ተቀንሰናል ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ

  ለአፍሪካ ጨዋታዎች የተመረጡ አትሌቶች ያለመስፈርት ተቀንሰናል ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ

  ቀን:

  የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በመጪው ነሐሴ በሞሮኮ ራባት ለሚከናወነው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች 85 ብሔራዊ አትሌቶችን በተለያየ የውድድር ዓይነት መርጦ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ ይሁንና ለሜዳ ተግባራትና ለአጭር ርቀት ከተመረጡት አትሌቶች መካከል 22ቱ ምክንያቱ ሳይነገራቸው መቀነሳቸውን ተናገሩ፡፡ ፌዴሬሽኑ በበኩሉ ቅነሳው በመግቢያ ሰዓት (ሚኒማ) ምክንያት መሆኑን ይናገራል፡፡ 12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ከሐምሌ 19 እስከ 23 ቀን 2011 ዓ.ም. እንደሚከናወን ይጠበቃል፡፡

  የተቀነሱትን አትሌቶች በመወከል ቅሬታቸውን ለሪፖርተር ካቀረቡት መካከል ከመከላከያ ስፖርት ክለብ በሜዳ ተግባራት የተቀነሰው ጌታቸው ተመስገን ይጠቀሳል፡፡ አትሌቱ እንደሚናገረው ከሆነ ዘንድሮ ለሚካሄደው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ለብሔራዊ ዝግጅት ጥሪ ተደርጎላቸው ሆቴል የገቡት ከአንድ ወር በፊት ነው፡፡ እሱን ጨምሮ በምርጫው የተካተቱት ሁሉም አትሌቶች ሚኒማ ባይኖራቸው ኖሮ ጥሪ ሊደረግላቸው እንደማይችል ያውቃሉ፡፡

  ለዚህ እንደ ማስረጃ የሚያቀርበው ደግሞ በምርጫው የተካተቱት ሁሉም አትሌቶች በኢትዮጵያ ሻምፒዮና ተካፍለው ደረጃ ውስጥ የገቡ መሆናቸው ነው፡፡ ይሁንና በአሠልጣኞችም ሆነ በሌላ በሚመለከተው አካል አንድም ቀን ሚኒማ  እንደማናሟላ ሳይነገረን፣ ከአንድ ወር በላይ በየቀኑ በልምምድ ሲያደክሙን ቆይተው መስፈርቱ ምን እንደሆነ ሳይታወቅ እንዲቀነሱ የተደረገበት አግባብ ትክክለኛ እንዳልሆነ አትሌቱ ይናገራል፡፡

  ሴቶችን በመወከል የተናገረችው እንስት በአሎሎ ውርወራ የተመረጠችው አመለ ይበልጣል በበኩሏ፣ በብሔራዊ ቡድን ዝግጅት በአቋም መውረድ አልያም በሚኒማ ቅነሳ የተለመደና የሚታወቅ ቢሆንም በእሷና በባልደረቦቿ የሆነው ግን ከመቼውም ጊዜ የማይወዳደር ፍጹም ተዓማኒነት የሌለው ድርጊት እንደሆነ ትናራለች፡፡ ምክንያቱን አስመልክቶም አትሌቷ፣ ‹‹እኔ በምወዳደርበት አሎሎ ውርወራ ሦስት ተመርጠን ሁለት ተቀንሰናል፣ የቀረችው አንዷ በምን መስፈርት እንደሆነ የምናውቀው ነገር የለም፣ ያውም ደግሞ በልምምድ ወቅት የሦስታችን ወቅታዊ አቋም ታይቶ ከሆነም ሊነገረን በተገባ ነበር፣›› በማለት ቅሬታዋን አቅርባለች፡፡

  የፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ዳይሬክተር አቶ ዱቤ ጅሎ በበኩላቸው፣ ‹‹አትሌቶቹ ከወር በፊት ሲመረጡ የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን (ሲኤኤ) የውድድሩን መግቢያ ሰዓት (ሚኒማ) አላከልንም፣ አሁን በቅርቡ ነው ሚኒማው የተላከልን፣›› ብለው የውድድሩ መግቢያ ሰዓት ከደረሳቸው በኋላ ግን አትሌቶቹ ባላቸው ሰዓት መሠረት ምርጫው መከናወኑን ተናግረዋል፡፡  

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት አልፈጸምኩም አለ

  የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ...

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...