Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፓርትበፎርፌዎች ለሩብ ፍጻሜ የበቃው የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜውም በፎርፌ እንዳይሆን ተሠግቷል

  በፎርፌዎች ለሩብ ፍጻሜ የበቃው የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜውም በፎርፌ እንዳይሆን ተሠግቷል

  ቀን:

  ከጥር ወር 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ከግማሽ በላይ ጨዋታዎችን በፎርፌ እያከናወነ የመጣው፣ የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜውም በፎርፌ እንዳይሆን አሁን ባለው ማረጋገጫ መስጠት እንደማይቻል እየተነገረ ይገኛል፡፡ መጠሪያውን ‹‹የኢትዮጵያ ዋንጫ›› ብሎ የፕሪሚየር ሊጉን ክለቦች በማሳተፍ ላይ የሚገኘው የውድድሩ መርሐ ግብር፣ እሑድ ሐምሌ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. አንድ ጨዋታ ካደረገ በኋላ ለግማሽ ፍጻሜ የሚበቁት አራት ቡድኖች ይለያሉ፡፡

  መጠሪያውን ‹‹የኢትዮጵያ ዋንጫ›› ብሎ ነገር ግን የፕሪሚየር ሊጉን ቡድኖች እያሳተፈ የሚገኘው ይህ መርሐ ግብር እስካሁን መደረግ ከነበረባቸው ጨዋታዎች ሦስቱን ብቻ አከናውኗል፡፡ የተቀሩት ጨዋታዎች በፎርፌ የተጠናቀቁ በመሆናቸው ስያሜውን እንደማይመጥንም ይነገራል፡፡ መሳተፍ ከነበረባቸው የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ደደቢት፣ ጅማ አባ ጅፋር፣ ደቡብ ፖሊስ፣ ድሬዳዋ ከተማ፣ ስሁል ሽረ ለተጋጣሚዎቻቸው ፎርፌ የሰጡ ናቸው፡፡

  ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የግማሽ ፍጻሜው ጨዋታ መቼ እንደሚከናወን ባይታወቅም፣ እሑድ ሐምሌ 7 ቀን በጎንደር አፄ ፋሲል ስታዲየም የሚጫወቱት የፋሲል ከተማና የአዳማ ከተማ አሸናፊ፣ ከፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ መቐለ 70 እንደርታ ጋር ተጫውቶ የፍጻሜው ተፋላሚ ይታወቃል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ ከሐዋሳ ከተማ ጋር በግማሽ ፍጻሜው የሚጫወት ይሆናል፡፡

  ይህንኑ ተከትሎ ለግማሽ ፍጻሜው ከደረሱት ቡድኖች መካከል ቀደም ሲል ለፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ ግምት የተሰጠው ፋሲል ከተማና ዋንጫውን ያነሳው መቐለ 70 እንደርታ ለኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ ለማለፍ የሚገናኙ ከሆነ፣ ምናልባትም ተጨማሪ ፎርፌ የሚሰጥ ቡድን ሊኖር እንደሚችል ይጠበቃል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች የወጣላቸውን መርሐ ግብር አክብረው ጨዋታቸውን የሚያከናውኑ ከሆነ ደግሞ ጨዋታው ከፍጻሜው በፊት የፍጻሜ ጨዋታ እንደሚሆን የሚጠብቁም በርካታ ናቸው፡፡

  በኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ የሚሆነው ቡድን ለአፍሪካ ክለቦች ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን ወክሎ በአኅጉራዊ መድረክ ይሳተፋል፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ የሆነው መቐለ 70 እንደርታ በጥንካሬው ጠንክሮበት ዋንጫውን የሚወስድ ከሆነ፣ ደግሞ ቀደም ሲል ባስመዘገበው ውጤት በአፍሪካ የክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊነቱን ያረጋገጠ መሆኑን ተከትሎ በፍጻሜው ሁለተኛ ሆኖ የሚያጠናቅቀው ቡድን በኮንፌዴሬሽኑ ዋንጫ ተሳታፊ ይሆናል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...