Wednesday, August 10, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየኢንሳ የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዋስትና ታገደ

  የኢንሳ የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዋስትና ታገደ

  ቀን:

  የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ሐምሌ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. በ30,000 ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም፣ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ለይግባኝ ሰሚው ችሎት ይግባኝ አቅርቦ እንዲታገድ አድርጓል፡፡

  በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት ቀድሞ የኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ምክትል ዳይሬክተር ሌተና ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ፣ በተመሠረተባቸው ክስ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቶባቸው ነበር፡፡

  የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007፣ አዋጅ ቁጥር 780/2005፣ አዋጅ ቁጥር 591/2007 የወንጀል ሕግ 808 ተላልፈዋል በማለት ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ በማስረዳቱ በአምስት ክሶች  እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቶ ነበር፡፡

  የተጠቀሱባቸው የሕግ ድንጋጌዎች ዋስትና እንደማይከለክሉ በማስረዳት ሌተና ኮሎኔል ቢኒያም በጠበቃቸው አማካይነት ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታቸውን እንዲጠብቅላቸው ጠይቀው ነበር፡፡

  ዓቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ የተጠቀሱት ሕጎች ከ15 ዓመታት በላይ ሊያስቀጧቸው እንደሚችሉ በመግለጽ፣ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ እንዲደረግ ተከራክሮ ነበር፡፡

  ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄው የሕግ ክልከላ ያለበት ነው ወይስ አይደለም የሚለውን መርምሮ፣ የዓቃቤ ሕግን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ በ30,000 ብር ዋስትና እንዲለቀቁና ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ የሚል ከሆነ በማለት አሥር ቀናት ለመጠባበቂያ ሰጥቶ ነበር፡፡

  ዓቃቤ ሕግም ይግባኙን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርቦ ‹‹ያስቀርባል›› በመባሉ፣ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እስከሚሰጥ ዋስትናው መታገዱ ታውቋል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የእናት ጡት ወተት የመጀመርያው የሕይወት ክትባት

  የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በዓለም ላይ ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶችን አስከትሏል፡፡ ከዚህ...

  ቻይናና ታይዋን የተወዛገቡበት የናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት

  የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን ለመጎብኘት...

  የአፍሪካ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ 13 የቴክኖሎጂ ዘርፎችን አካቶ ሊካሄድ ነው

  አሥራ ሦስት የተለያዩ የቴክኖሎጂ ዘርፎችን ያካተተ የአፍሪካ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ...

  ‹‹ምዕራባውያን አፍሪካውያንን ለማዘዝ የሚያሳዩት ፍላጎት ተቀባይነት የለውም››

  የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንደር የአሜሪካ የውጭ...