Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፓርትስለተጨዋቾች የደመወዝ ዕርከን ለመምከር ቀጠሮ ከያዙ ክለቦች አብዛኞቹ ሳይገኙ ቀሩ

  ስለተጨዋቾች የደመወዝ ዕርከን ለመምከር ቀጠሮ ከያዙ ክለቦች አብዛኞቹ ሳይገኙ ቀሩ

  ቀን:

  የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈዴሬሽን በባለቤትነት ከሚመራቸው ውድድሮች የከፍተኛ (ሱፐር) ሊግና የብሔራዊ ሊግ ክለቦች የሚሳተፉበት ሊግ ይጠቀሳሉ፡፡ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የተጨዋቾችን ወርኃዊ የደመወዝ ጣሪያን አስመልክቶ ከሁለት ሳምንት በፊት ቢሾፍቱ ላይ ተወያይተው ውሳኔ ላይ መድረሳቸው ይታወሳል፡፡ በከፍተኛውና በብሔራዊ ሊግ የሚሳተፉ ክለቦችም በተመሳሳይ በጉዳዩ ተወያይተው ውሳኔ እንዲያሳልፉ ጥሪ ከተደረገላቸው 91 ክለቦች ውስጥ 31 ብቻ በመገኘታቸው ውይይቱ ሳይደረግ ፕሮግራሙ ወደ ሌላ ቀን እንዲተላለፍ መደረጉን ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡

  በስፖርታዊ ጨዋነት መጓደልና በተያያዥ ችግሮች የተነሳ ፕሪሚየር ሊጉን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ በተለይም ዘንድሮ የተጠናቀቀው በአጨቃጫቂና በአሰልቺ ሁኔታ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በዚህ መነሻነት ይመስላል የአዲስ አበባዎቹ ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና የውድድሩ ቅርፅና ይዘት ለአገሪቱ የእግር ኳስ ዕድገት መቀጨጭ ብቻ ሳይሆን፣ በክለቦች ፋይናንስ እንዲሁም ለዜጎች የዕለት ተዕለት ማኅበራዊ መስተጋብር ላይ እያስከተለ ያለው ችግር ከፍተኛ እየሆነ በመምጣቱ በነበረው እንደማይቀጥሉ ያስታወቁት፡፡

  ሁለቱ ክለቦች የደረሱበትን አቋም በሚመለከት ምንም ዓይነት መግለጫም ሆነ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቦ የቆየው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ ለክለቦች ሕልውና አደጋ በሆነው የተጨዋቾች ወርኃዊ ክፍያ ላይ በተለይ ከፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ጋር ተወያይቶ በራሳቸው በክለቦቹ ፍላጎትና ውሳኔ መሠረት የክፍያው ጣሪያ 50.000 (ሃምሳ ሺሕ) ብር እንዲሆን መስማማቱ ይታወሳል፡፡ ይሁንና የሁለቱ ክለቦች ዋነኛ ተግዳሮት የተዟዙሮ ጨዋታ አንዱና ዋነኛው ጥያቄ መሆኑ ችግሩን ‹‹ከድጡ ወደ ማጡ›› ማድረጉ እንደማይቀር የሚናገሩ አሉ፡፡

  ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ጋር የደረሰበትን የደመወዝ ጣሪያ ከብሔራዊና ከከፍተኛው ሊጉ ክለቦች ጋር ተመሳሳይ ውይይት አድርጎ ጉዳዩ መቋጫ ያገኝ ዘንድ ባለፈው እሑድ ነሐሴ 12 ቀን 2011 ዓ.ም. በዓለም ገና አንኳር ሆቴል የጠራው ለስብሰባ የመጡት ክለቦች ውይይቱን ለማድረግ የማያስችል በመሆኑ ፕሮግራሙ እንዲተላለፍ ተደርጓል፡፡

  በሁለቱ ሊጎች ማለትም ከብሔራዊ ሊጉ 56 ክለቦች ሲገኙ፣ በከፍተኛው ሊጉ ደግሞ 36 ክለቦች አሉ፡፡ ፌዴሬሽኑ በጠራው ስብሰባ የተገኙት ከከፍተኛው 20 እና ከብሔራዊ ሊግ ደግሞ 15 መሆናቸው ታውቋል፡፡ እንደ ፌዴሬሽኑ መግለጫ ከሆነ ጉዳዩ የግድ መቋጫ ማግኘት ስለሚኖርበት ለነሐሴ 25 ቀን ሌላ ቀጠሮ ይዟል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...