Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ኪንና ባህልማሞ ቂሎን በሞባይል ጌም

  ማሞ ቂሎን በሞባይል ጌም

  ቀን:

  በድሮ ዘመን አንድ ንጉሥ ነበር። ይህም ንጉሥ አንድ ሞኝ አጫዋች ነበረው። ንጉሡ በሚያዝንበትና በሚተክዝበት ጊዜ ሁሉ ይህንን ሞኝ አጫዋች እየጠራ ሐዘኑንና ትካዜውን የሚያርቅበትን ጨዋታ ያዳምጥ ነበረ። ንጉሡም በዚህ ሞኝ ጨዋታ ደስተኛ ነበረ፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ግን የንጉሡ ልጅ ታመመች፡፡ የማሞ አያትም ለንጉሡ ልጅ መድኃኒት እንዲያደርስ ማሞን ይልኩታል፡፡ ማሞም ይህን መልዕክት ለማድረስ ብዙ መሰናክሎች ያጋጥሙታል፡፡

  ይህንንም መሠረት በማድረግ፣ ከአንድ ዓመት በፊት በአራት ወጣቶች የተመሠረተው እንጫወት ጌምስ በኤደብሊው ዌብ ሰርቪስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር አማካይነት የመጀመርያውን ‹‹ማሞ›› የተሰኘውን ጌም አቅርበዋል፡፡ በዚህ ሞባይል ጌምም ማሞ ከቤቱ ጀምሮ ንጉሡ ለመድረስ የሚያየውን ውጣ ውረድ ይዳስሳል፡፡ ሁሉም የጌሙ ተጫዋች ማሞን በመሆን የውጣ ውረዱ ተካፋይ እንዲሆን ያደረገው ልጆች ከልጅነታቸው ጀምሮ የሕይወትን ውጣ ውረድ በማዝናናት መልኩ እንዲማሩ ነው፡፡ ብዙ መውደቅ ቢኖርም በጊዜ ሒደት ማለፍ እንደሚቻል ጌሙ ከማሳየቱም ባሻገር ልጆች ልዩ ልዩ ታሪኮችን በጌም እንዲያውቁ ያደርጋል፡፡

  ይህ ማሞ የተሰኘው ሞባይል ሐምሌ 13 ቀን 2011 ዓ.ም. ቦሌ በሚገኘው ዳይመንድ ሆቴል የተመረቀ ሲሆን፣ በዚሁ ሳምንት መጨረሻ ላይ ፕሌይስቶር ላይ ማግኘት እንደሚቻል ተገልጻል፡፡

  ‹‹አምስት ደረጃ ያለው ይኸው ጌም ፈተናዎቹ በቀላል የሚታለፉ አይደሉም፤›› የሚለው ከመሥራቾቹ አንዱ የሆኑት አቶ ዓብይ ኃይሉ ናቸው፡፡ ‹‹በቀላሉ ይታለፋል ተብለው የታሰቡት ፈታኝ ሆነው ይገኛሉ፤ በዚህም ጊዜ ማለፍ ያቃተውን ሰው ‹ማሞ ቂሎ› በማለት ሲጥለው፣ ማለፍ የቻለውን ሰው ደግሞ በተቃራኒው ‹ማሞ ብልጦ› በማለት ያሞግሰዋል፤›› ብለዋል፡፡

  ልጆች ላይ መሥራት ለአገር ሚያተርፈው ብዙ ነው ያሉት አቶ ዓብይ፣ ከተለያዩ አካላት ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸዋል፡፡ አገርን ከማስተዋወቅ አንፃርም ጌሙ ዓይነተኛ ሚና እንደሚጫወት በመናገር ‹‹ይዘን የቀረብነው ሐሳብ ሊደገፍ የሚገባው ነው፤›› በማለት ድጋፍ የሚሹት ከመንግሥት፣ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እንዲሁም ከኅብረተሰቡ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

  ስለ ጌሙም ሲያስረዱ ደረጃ አንድንና ሁለትን ለመጫወት ምንም ክፍያ ለማንም እንደማያስከፍሉ በማስረዳት ደረጃ ሦስት፣ አራት እንዲሁም አምስትን ግን በአነስተኛ ክፍያ መጫወት እንደሚቻል፣ ነገር ግን መጫወት የሚችሉት ከአገር ውጪ ያሉ ሰዎች እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያትንም ኢትዮጵያ ውስጥ ሲስተሙ ክፍት ባለመሆኑ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ጌሙን ለመደገፍ ለሚፈልጉ ከአገር ውጪ ለሚኖሩ ሰዎች የጎ ፈንድ ሚ (Go Fund Me) ሒሳብ እንደከፈቱ በመግለጽ ሒሳቡ ጎ ፈንድ ሚ ማሞ (Go Fund Me Mamo) እንደሚል ተናግረዋል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...