Monday, August 15, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናከ60 በላይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅን ተቃወሙ

  ከ60 በላይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅን ተቃወሙ

  ቀን:

  በቅርቡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ የፀደቀው የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ በአገሪቱ ለአንድ ዓመት ያህል ለቀቅ ተደርጎ የነበረውን የፖለቲካ ነፃነት፣ በተለይም ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ምሥረታ እጅግ አስፈላጊ የሆነውን በፖለቲካ ፓርቲዎች የመደራጀት ነፃነትና የዜጎችን በነፃነት የመምረጥና የመመረጥ መብትን የሚነፍግ፣ የፖለቲካ ምኅዳሩንም የሚዘጋና ወደ አምባገነናዊ ቁልቁለት የሚወስድ ሕግ ነው በማለት 65 የፖለቲካ ፓርቲዎች በአዋጁ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ አሰሙ፡፡

  ፓርቲዎቹ በአዋጁ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ያሰሙት ማክሰኞ ጳጉሜን 5 ቀን 2011 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ጽሕፈት ቤት፣ ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ በነፃነት የመደራጀት መብቱን ሊቀማ አይገባም›› በማለት በሰጡት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡

  ‹‹በአገራችን የተጀመረው የለውጥ ሒደት መንግሥት ቃል በገባው መሠረት የፖለቲካ ምኅዳሩን የሚያሰፋ መሆን ነበረበት፡፡ የሚደረጉና የተደረጉ የሕግ ማሻሻያዎችም የፖለቲካ ምኅዳሩን የሚያሰፉና አሳታፊ የሚያደርጉ ሊሆን ይገባ ነበር፡፡ እኛ የኢትዮጵያ ዜጎች የታገልነው፣ የደምና የሕይወት መስዋዕትነት የከፈልነው ሰብዓዊና ዴሞክራሲዊ መብት እንዲከበር፣ የዜጎች በነፃነት የመንቀሳቀስ፣ የመደራጀት፣ የመምረጥና የመመረጥ፣ በየትኛውም ቦታና ጊዜ በነፃነት ሀብት ንብረት አፍርቶ የመኖር መብትና ነፃነታችን እንዲጠበቅና እንዲከበር እንጂ፣ ጨቋኝ ያልነው ሕግ ተሽሮ አፋኝና ፀረ ዴሞክራሲ የሆነ ሕግ እንዲሠለጥንብን አይደለም፤›› በማለት 65 ፓርቲዎችን የወከሉ አመራሮች በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡

  በአገሪቱ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት ታላቅ ሚና ይጫወታል ተብለው ከሚታሰቡና ከሚታመኑ የዴሞክራሲ ተቋማት አንዱ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መሆኑን በመጥቀስ፣ ‹‹ነገር ግን አንዳንድ የቦርዱ ኃላፊዎች በምርጫና በፖለቲካ ፓርቲዎች ሕግ ላይ ፓርቲዎች ደጋግመው ያቀረቡትን የማሻሻያ ሐሳብ ካለመቀበላቸውም በላይ፣ ሕጉ ገና ፀድቆ ሳይወጣ ጀምሮ አፋኝና ፀረ ዴሞክራሲያዊ ለሆነው ረቂቅ ሕግ ወገንተኛ ሆነው መቆማቸው ሲታይ በአገሪቱ ከገዥው ፓርቲ በላይ ዴሞክራሲያዊ ሒደቱን ለማፈን ምን ያህል የተዘጋጀና የተጠማ ኃይል በተቋሙ ውስጥ እንደተሰበሰበ አሳይቶናል፤›› በማለት የምርጫ ቦርድ ኃላፊዎችንም በመግለጫቸው ወቅሰዋል፡፡

  ስለሆነም የፀደቀው የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሕግ የዜጎችን መሠረታዊ የመደራጀት፣ መምረጥና የመመረጥ፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትን የጣሰ አፋኝ ሕግ በመሆኑ ሥራ ላይ እንዳይውል ሲሉ ፓርቲዎቹ አጥብቀው ጠይቀዋል፡፡

  አዋጁ ዳግም ለውይይት ወደ ጠረጴዛ እንዲመለስ፣ እንዲሁም መላው ኢትዮጵያ ሕዝብና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሕጉ እንዲሻሻል ግፊትና ጫና እንዲያደርጉ በመጠየቅ በቅርቡ ‹‹የድምፃችን ይሰማ ሕዝባዊ ንቅናቄ›› እንደሚጀምሩ ፓርቲዎቹ አስታውቀዋል፡፡ 

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...