Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፓርትከውይይት መድረክነት ያልተሻገረው የማዘውተሪያዎች ዕጣ ፈንታ

  ከውይይት መድረክነት ያልተሻገረው የማዘውተሪያዎች ዕጣ ፈንታ

  ቀን:

  መንግሥት የስፖርት ማዘውተሪያዎችን በሚመለከት ጥበቃ እንዲደረግላቸው የሚያስገድዱ የተለያዩ ደንብና መመሪያዎችን ካወጣ ዓመታት ቢቆጠሩም፣ መመሪያው ሼልፍ ማድመቂያ ከመሆን ያለፈ ሚና ሳይኖረው የማዘውተሪያ ጉዳይ አሁንም እያነጋገረ ይገኛል፡፡ ከሰሞኑ ከስፖርቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው የሪፎርም ፕሮግራሞችን የተመለከቱ ውይይቶች በአዳማ ከተማ መካሄዱን ስፖርት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

  ኮሚሽኑ በአዳማ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ፣ ‹‹የስፖርት ሜዳዎችን መንጠቅ ማለት የዜጎችን በስፖርት የመሳተፍ መብት መጋፋት ነው›› በሚል መሪ ቃል መካሄዱ ኮሚሽኑ በድረ ገጹ አስታውቋል፡፡ በወረቀት ካልሆነ በተግባር የማይታወቀው የስፖርት ሪፎርም ፕሮግራምን ለማስተግበር፣ ለስፖርት አመራሮች፣ ለባለሙያዎችና ጉዳዩ በአንድም ሆነ በሌላ በሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በውይይቱ መታደማቸው ተነግሯል፡፡

  ጥርት ያለ የተጠሪነት ወሰን እንደሌለው የሚነገርለት የኢትዮጵያ ስፖርት፣ ለዓመታት አንዴ ከባህል ሌላ ጊዜ ደግሞ ወጣቶችና ስፖርት፣ በመሐል ስፖርት ኮሚሽን ተብሎ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ሲሆን፣ በቅርቡ በተደረገው የአመራር ለውጥ ስፖርቱ እንደገና ቀድሞ እንደነበረው ተጠሪነቱ ለባህልና ቱሪዝም መሆኑ የችግሩ አንዱ ማሳያ አድርገው የሚወስዱት አልጠፉም፡፡

  የስፖርት ሪፎርም ፕሮግራምን በሚመለከት በውይይት መድረኩ ማብራሪያ እንዲሰጡ የተጋበዙት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር አቶ ሳሙኤል ስለሺ ሲሆኑ፣ የውይይቱ መደምደሚ ወደ መሬት የሚወርድ ከሆነ ለስፖርቱ ትልቅ ነገር እንደሆነ የሚናገሩ አሉ፡፡ እንደ አስተያየት ሰጪዎቹ ከሆነ የኮሚሽኑ የተጠሪነት ወሰን አሁንም ያልጠራ መሆኑ እንደተጠበቀ፣ አሳሳቢነቱ ከቀን ወደ ቀን እየባሰበት የመጣው የስፖርት ማዘውተሪያ ዕጦትና እጥረት ጉዳይ በተወሰነ መልኩ መፍትሔ ሊያገኝ የሚችልበት አጋጣሚ ሊኖር እንደሚችል ተስፋ አላቸው፡፡

  በቅርቡ የስፖርት ኮሚሽነር በመሆን የተሾሙት አቶ ኤልያስ ሽኩር ውይይቱን በንግግር ሲከፍቱ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የኢትዮጵያን ስፖርት ዕድገት ለማፋጠንና ጥራቱ የተጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት በርካታ ባለሙያተኞች የተሳተፉበት የስፖርት ሪፎርም ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ለብሔራዊ ስፖርት ምክር ቤት ቀርቦ የጸደቀ መሆኑን በማስታወስ፣ ሰነዱን ወደ ተግባር ለመቀየር ለሚመለከተው አካል ግንዛቤ መፍጠር በማስፈለጉ መድረኩ ስለመመቻቸቱ መናገራቸው ታውቋል፡፡

  የመድረኩ አስፈላጊነት ለድርድር እንደማይቀርብ የሚናገሩ አንዳንድ ታዳሚዎች ለሪፖርተር እንደሚገልጹት ከሆነ፣ ከዚህ በፊትም የዚህ ተመሳሳይ የውይይት መድረኮች ተዘጋጅተው ማዘውተሪያዎችን ጨምሮ ለኢትዮጵያ ስፖርት ተግዳሮት ተብለው በሚጠቀሱ በርካታ አጀንዳዎች ላይ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበዋል፡፡ ይሁንና በትናንቱ ውጤት መሠረት ዕቅዶች ስለማይተገበሩ ለውጥ ሊመጣ እንዳልቻለ ሁሉ፣ አሁንም የውይይቱ ርዕሰ ነጥብ ቅቡልነቱ መሪ ቃሉ ካልሆነ ወደ መሬት የመውረዱ ነገር በጥርጣሬ የሚመለከቱት ጉዳይ ነው፡፡

  በኮሚሽኑ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በስፖርት ሳይንስ ከመጀመሪያ እስከ ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው በርካታ ባለሙያዎች እንዳሉ የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች፣ ኮሚሽኑ ይህን ኃይል አግባብ ባለው መልኩ ሊጠቀምበት እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡

  በኮሚሽኑ በርካታ ባለሙያዎች እንዳሉ ቢነገርም፣ በስፖርቱ አካባቢ ላሉት ክፍተቶች መፍትሔ በማፈላለግ ረገድ የጎላ ሚና መጫወት ቢገባቸውም፣ የሚጠበቅባቸውን እየተወጡ አይደሉም የሚል ትችት ይሰነዘርባቸዋል፡፡ አንዳንዶች በስፖርቱ አካባቢ ወቅቶችን እየጠበቁ ለሚፈጠሩ ትርምሶች መንስዔ መሆናቸው አልቀረም፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...