Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየፌዴራልን ጨምሮ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ፖሊስ የተዋቀረ ግብረ ኃይል ሕገወጥ የመሬት ወረራን...

  የፌዴራልን ጨምሮ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ፖሊስ የተዋቀረ ግብረ ኃይል ሕገወጥ የመሬት ወረራን እንዲያፀዳ መመርያ ተሰጠው

  ቀን:

  ዘመቻው ከጥር 2 ቀን 2012 ዓ.ም. አንስቶ ይጀመራል

  ባለፉት አራት ወራት 2,317 ይዞታዎች ወረራ ተፈጽሞባቸዋል

  ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከኦሮሚያ ክልል መንግሥትና ከአዲስ አበባ አስተዳደር የፖሊስ ኮሚሽኖች ተወጣጥቶ የተዋቀረ ሕግ አስከባሪ ግብረ ኃይል በሁሉም የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች የተፈጸሙ ሕገወጥ የመሬት ወረራዎችን እንዲያፀዳ መመርያ ተሰጠው።

  በመመርያው መሠረትም ግብረ ኃይሉ ከጥር 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ የሕግ ማስከበር ዘመቻውን፣ በ116 የአዲስ አበባ ወረዳዎች እንደሚጀምር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ለሪፖርተር አረጋግጠዋል።

  የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የኦሮሚያ ፖሊስና የአዲስ አበባ አጎራባች ከተሞችና ወረዳዎች አመራሮችን አጣምሮ የያዘው ግብረ ኃይል በተቀናጀና በተጠናከረ መንገድ ሕግ የማስከበር ዘመቻውን በመጀመር፣ ሕገወጥ የመሬት ላይ ግንባታዎችን እንደሚያፀዳና በማያዳግም ሁኔታ ኃላፊነቱን እንደሚወጣ አስረድተዋል።

  ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በበርካታ የከተማዋ ወረዳዎች ሕገወጥ የመሬት ወረራ መስፋፋቱን፣ ሪፖርተር ከከተማ አስተዳደሩ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

  በማስፋፊያነት የተለዩ የመንግሥት ይዞታዎች፣ ለአልሚዎች ተላልፈው ግንባታ ያልተጀመረባቸው ይዞታዎች ላይ በየዕለቱ የላስቲክና የቆርቆሮ ቤቶች ተሠርተውባቸው እንደሚያድሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። በከፊል የአርሶ አደር የሆኑ ይዞታዎችን፣ እንዲሁም በሊዝ ከተፈቀደላቸው ውጪ የሚገኙ ቁራጭ ይዞታዎችን አካተው ያጠሩ መኖራቸውንም መረጃው ያስረዳል።

  በአሁኑ ወቅት በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች በሕገወጥ መንገድ የተያዙ መሬቶችንና የተገነቡ ቤቶችን የመለየት ሥራ በመገባደድ ላይ እንደሆነ ታውቋል፡፡

  በተለይ በአስተዳደሩ አምስት ክፍላተ ከተሞች ሕገወጥ የመሬት ወረራና ግንባታዎች በስፋት ከተከናወኑባቸው መካከል እንደሆኑ መረጃው ያመለክታል።

  እነዚህ አምስት ክፍላተ ከተሞችም ኮልፌ ቀራኒዮ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ቦሌ፣ አቃቂ ቃሊቲና የካ ክፍላተ ከተሞች ናቸው።

  በእነዚህ ክፍላተ ከተሞች በአራት ወራት ውስጥ ብቻ ከ2,317 በላይ ይዞታዎች በሩብ ዓመት ውስጥ በሕገወጥ መንገድ ተወረው እንደተገኙ፣ ከከተማ አስተዳደሩ ደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤት ለመረዳት ተችሏል፡፡

  ከእነዚህ ውስጥ 1,371 የሚሆነው የመሬት ወረራ የተፈጸመው በየካ ክፍለ ከተማ እንደሆነም ታውቋል።

  ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ አቃቂና ቦሌ እንደ ቅደም ተከተላቸው የመሬት ወረራ የተስፋፋባቸው አካባቢዎች ናቸው ተብሏል፡፡

  “ከሕገወጥ ግንባታው ጀርባ ያሉትን የምንለይበት ቀን ሩቅ አይሆንም፤” ሲሉ ምክትል ከንቲባ ታከለ ለሪፖርተር ገልጸዋል።

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት አልፈጸምኩም አለ

  የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ...

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...