Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፓርትባለሥልጣኖችና ርዕሳነ መምህራን የተሳተፉበት የኦሊምፒክ ተሳትፎ ንቅናቄ ተጀመረ

  ባለሥልጣኖችና ርዕሳነ መምህራን የተሳተፉበት የኦሊምፒክ ተሳትፎ ንቅናቄ ተጀመረ

  ቀን:

  የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በየአራት ዓመቱ አንድ ጊዜ የሚያዘጋጀው ትልቁ የስፖርት መድረክ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በጃፓን አስተናጋጅነት ሊካሄድ የቀረው የጥቂት ወራት ዕድሜ ብቻ ነው፡፡ በመድረኩ የሚሳተፉ አገሮች ዝግጅቶቻቸውን በይፋ ጀምረዋል፡፡ ተሳትፎዋን በሜልቦርን ኦሊምፒክ አንድ ብላ የጀመረችው ኢትዮጵያ በመጪው ክረምት በቶኪዮ እንደሚካሄድ በሚጠበቀው ኦሊምፒክ ላይ ለምታደርገው ተሳትፎ በብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው በኩል ዝግጅቷን ጀምራለች፡፡ 

  ኢትዮጵያ አበበ ቢቂላ በባዶ እግሩ በሮም ኦሊምፒክ “ሀ” ብላ የጀመረችው የአሸናፊነት መንፈስ በተለይም በአትሌቲክሱ ትልቅ ዕውቅና ካላቸው በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ አገሮች አንዷ እንድትሆን የተጫወተው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ይታመናል፡፡

  የጃፓኗ ቶኪዮ ለሁለተኛ ጊዜ በመጪው ክረምት በሚካሄደው ቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የታላቁን አትሌት ገድል የሚመጥን ተሳትፎ ለማድረግ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እያከናወነ ከሚገኘው እንቅስቃሴ መካከል ኅብረተሰቡ በእኔነት ስሜት በቅድመ ዝግጅቱ የሚሳተፍበትን ሁኔታ ማመቻቸት አንዱ ነው፡፡

  ‹‹የኦሊምፒዝም እንቅስቃሴ ለማኅበራዊ ፋይዳ›› በሚል ማክሰኞ ጥር 19 ቀን 2012 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራንና መምህራን እንዲሁም የቀድሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር) እና ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የተሳተፉበት መድረክ በግዮን ሆቴል ተዘጋጅቶ፣ ኢትዮጵያ በቀጣዩ የቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ ስለሚኖራት ተሳትፎ ውይይት አድርገዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከ“ቶኪዮ እስከ ቶኪዮ” ያስመዘገበችው ውጤት በሒደት ከመሻሻል ይልቅ እያሽቆለቆለ መምጣቱ ለምን? የሚሉ ሐሳቦች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

  ዝግጅቱን በሚመለከት ከዚህ በፊት ኦሊምፒክ ሲቃረብ ካልሆነ እንዲህ እንደ አሁኑ የሥርዓቱ መሠረት የሆኑ ትምህርት ቤቶችን፣ ጨምሮ ሌሎችም የኅብረተሰብ ክፍሎች በእኔነት ስሜት የሚሳተፉበት ሁኔታ ባለመኖሩ ስፖርቱን ከባህልና ትምህርት እንዲሁም በኦሊምፒክ እንደሚነገረው የሕይወት ፍልስፍና አንድ አካል አድርጎ ለመጓዝ እንዳልተቻለ በመድረኩ ተነግሯል፡፡

  በዚህም ኦሊምፒዝምን በኢትዮጵያ በማስፋፋት፣ የኦሊምፒክ እሴቶችና መርሆዎች ላይ በቂ ግንዛቤ እንዳይፈጠር ምክንያት ሆኖ ስለመቆየቱ ጭምር በውይይቱ ተነስቷል፡፡

  መድረኩ ኦሊምፒክ ሲቃረብ ብቻ ሳይሆን፣ አሁን እንደተጀመረው መቀጠል እንዳለበት በመድረኩ ከመንፀባረቁም በላይ በተለይ የስፖርት መሠረት ትምህርት ቤቶች ላይ ትኩረት አድርጎ መሠራት እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡

  በውይይቱ የታደሙት አቶ አባዱላ ገመዳ በበኩላቸው፣ ‹‹አሁን የሁላችንም ትኩረት መሆን ያለበት ከፊት ለፊታችን ለሚጠብቀን የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ነው፡፡ በተለይም ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸው ላይ ሠርተው በጎ ገጽታ መፍጠር የሁላችንም ኃላፊነት መሆን ይጠበቅበታል፤›› ብለው ይህ ኦሊምፒክ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ተከትሎ ወጣቱ ወደ ትክክለኛው መስመር እንዲመለስ ማድረግና ኦሊምፒክ  ከማናቸውም ሃይማኖት፣ ፖለቲካና ዘር ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ሳይኖረው ነፃ የሆነ ሰላማዊ እንቅስቃሴ የሚደረግበት መድረክ ስለመሆኑ ጭምር ተናግረዋል፡፡

  ኦሊምፒክን እንርዳ ሲባል ሚሊዮኖችን አትሌት ለማድረግ፣ ነገር ግን አትሌቶችን በመደገፍ ለተሻለ ውጤት በማብቃት የአገሪቱን ስምና መልካም ገጽታ እንዲያስጠሩ የግድ መሆኑን ያስረዱት አቶ አባዱላ፣ ‹‹ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማውን ነዋሪ በማነቃነቅ የፈጠረው ቤተሰባዊ ግንኙነትና ትስስር በተለይም ኅብረተሰቡ ጤናውን እንዲጠብቅ፣ አንድነቱን እንዲያጠናክር፣ ትልቅ መነቃቃት ሆኖለት አልፏል፤›› ብለዋል፡፡ ይህ ዛሬ የተጀመረው ኦሊምፒክን የማስረፅ ንቅናቄ ወደ ሌሎች ክልሎች የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለማስፋፋት የኦሊምፒክ ችቦ የካቲት 8 ቀን 2012 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ እንደሚነሳም በውይይቱ ተነግሯል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...

  ሰበበኞች!

  ዛሬ የምንጓዘው ከሜክሲኮ ወደ አየር ጤና ነው፡፡ ዛሬም፣ ነገም...