Monday, August 15, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናአብሮነት የሽግግር መንግሥት ጥያቄ ቋሚ የትግል አጀንዳው መሆኑን አስታወቀ

  አብሮነት የሽግግር መንግሥት ጥያቄ ቋሚ የትግል አጀንዳው መሆኑን አስታወቀ

  ቀን:

  በሦስት የተቃውሞ ጎራው ፓርቲዎች አማካይነት የተመሠረተው አብሮነት ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት (አብሮነት)፣ የሽግግር መንግሥት ጥያቄ ቋሚ የትግል አጀንዳው መሆኑን አስታወቀ፡፡

  የትብብር ስብስቡ አባል ፓርቲዎች ይህን አቋማቸውን ይፋ ያደረጉት ሰኞ ግንቦት 10 ቀን 2012 ዓ.ም.፣ ‹‹የሽግግር መንግሥት ጥያቄ ቋሚ የትግል አጀንዳችን ሆኗል›› በሚል ርዕስ ባወጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አማካይነት ነው፡፡

  ትብብሩን ከመሠረቱት ፓርቲዎች አንዱ የሆነው ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ልደቱ አያሌው በመጋቢት ወር፣ ‹‹ህዳሴ የዕርቅና የአንድነት የሽግግር መንግሥት›› የሚል ዘለግ ያለ ሰነድ በማዘጋጀት የሽግግር መንግሥትን አስፈላጊነት ሲሞግቱ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

  ሆኖም በወቅቱ ‹‹ሰነዱ በኢዴፓና በአብሮነት ውይይት ተካሂዶበት የድርጅት ሰነድ ከመሆኑ በፊትና ለመንግሥት በጥያቄ መልክ ከመቅረቡ በፊት ይህ ረቂቅ ለመገናኛ ብዙኃንና ለሕዝብ ይፋ ተደርጎ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ግብዓት ቢገኝ ጠቃሚ እንደሚሆን ስለሚታመንበት፣ በዚህ መልክ ይፋ እንዲሆን ተደርጓል፤›› የሚል ማሳሰቢያ ይዞ ነበር፡፡

  በዚህም መሠረት ሰኞ ዕለት የወጣው የአብሮነት መግለጫ እንደሚገልጸው፣ በሰነዱ ላይ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የአብሮነት አባላት መወያየታቸውን፣ ከዚህ በተጨማሪም ‹‹700 አስተያየቶች›› በኢሜይል አማካይነት መሰብሰባቸውን በመግለጽ፣ ‹‹የዕርቅና የአንድነት የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም የሚጠይቀው ሰነድ የጋራ ሰነዳቸው እንዲሆን ተቀብለውታል፤›› በማለት፣ ከወራት በፊት የቀረበው ሰነድ አሁን የጋራ መታገያ ሰነዳቸው መሆኑን ይፋ አድርገዋል፡፡

  በጋራ የተቀበሉት ሰነድ ላይ መጠነኛ ማሻሻያ ማድረጋቸውን ያስታወቁት ፓርቲዎቹ፣ በዋነኛነት በሁለት ጉዳዮች ላይ ማሻሻያ ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡ እነዚህም ከዚህ ቀደም ከነበሩት ጥያቄዎች በተጨማሪ፣ አገር አቀፍ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ጉዳይ አወዛጋቢ የፖለቲካ አጀንዳ እየሆነ በመምጣቱ የሽግግር መንግሥቱ አንዱ ኃላፊነት የሕዝብና ቤት ቆጠራ ማካሄድ እንዲሆን፣ እንዲሁም ደግሞ የሽግግር መንግሥቱ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ረቂቅ የማቅረብ ብቻ ሳይሆን፣ ‹‹በሕዝብ ውሳኔ ሕገ መንግሥት የማሻሻል ኃላፊነት እንዲኖረው፤›› የሚል ነው፡፡

  ‹‹አገራችን ኢትዮጵያ ከእንግዲህ መዋቅራዊ ችግሮቿን በአስተማማኝ ሁኔታ ሊፈታ በሚችል ውጤታማ የሽግግር ሒደት ውስጥ ማለፍ እስካልቻለች ድረስ፣ እንደ ተለመደው በየአምስት ዓመቱ የይስሙላ ምርጫ በማካሄድ ወደ መዋቅራዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ልትሸጋገር አትችልም፤›› የሚል መደምደሚያ ላይ መድረሱን አብሮነት አስታውቋል፡፡

  በመሆኑም አገሪቱን ከእንዲህ ዓይነት ‹‹አስፈሪ ጥፋት›› መታደግ የሚቻለው፣ ‹‹በቂ ሥነ ልቦናና የመዋቅር ዝግጅት ያልተደረገበት አገራዊ ምርጫ በማካሄድ ሳይሆን፣ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ሁሉን አቀፍ የሆነ የዕርቅና የአንድነት የሽግግር መንግሥት በማቋቋም ነው፤›› ሲል የአገሪቱ ችግሮች የሚፈቱት በሽግግር መንግሥት እንደሆነ በመግለጽ፣ በጉዳዩ ላይ ያለውን ፅኑ እምነት አስታውቋል፡፡

  አብሮነት በኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) በኅብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኅብረ ኢትዮጵያ)፣ እንዲሁም ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መሰረዙ የተገለጸው የኢትዮጵያውያን አገር አቀፍ ንቅናቄ (ኢሃን) አማካይነት አገራዊ ህልውናን ማስጠበቅ የሚል አጀንዳ ለማራመድ የተቋቋመ የትብብር ስብስብ መሆኑ ይታወሳል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...