Friday, August 19, 2022
ሌሎች ዓምዶች

  የአሜሪካ ሊቀመንበርነትን ተከትሎ ወደ ፀጥታው ምክር ቤት እየሄደ የሚገኘው የትግራይ ክልል ሰብዓዊ ቀውስና አንድምታው

  - Advertisement -spot_img

  በብዛት የተነበቡ

  ‹‹ሁሉም የሰብዓዊ መብቶች የተረጋገጡባት፣ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች የሚከበሩባትና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚፈጽሙ በሕግ ተጠያቂ የሚሆኑባት ዓለም እንድትፈጠር አሜሪካ አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ ናት።›› 

  የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ብሊንከን አሜሪካ የማርች ወር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ሊቀመንበር ሆና ለመመረጥ የስድስት ቀናት ዕድሜ በቀሩበት፣ እ.ኤ.አ. ፌብሯሪ 24 ቀን 2021 ያደረጉት ንግግር ነው። 

  አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባይደን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸው አንዱ ማዕከል ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትንና ሰብዓዊ መብቶች በመላው ዓለም እንዲረጋገጡ ማድረግ እንደሆነ የተናገሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ ነገር ግን አሜሪካ ይህ ብቻዋን ማሳካት እንደማትችል ገልጸዋል።

  አሜሪካ ይህንን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ መሠረታዊ ማዕከል አድርጋ ያስቀመጠችውን ሰብዓዊ መብቶችን በመላው ዓለም እንዲከበሩ ለማድረግ፣ ከወዳጆቿናአጋሮቿ ጋር እንደምትሠራ ተናግረዋል።

  ሰኞ ዕለት ለጀመረው የማርች ወር የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ሊቀመንበር በመሆን የተመረጠችው አሜሪካየተመድ አምባሳደር አድርጋ በሰየመቻቸው ጥቁር አሜሪካዊቷ ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ በኩል የሊቀመንበርነት ሥልጣኑን ተረክባለች።

  አሜሪካ የተመድ የፀጥታ ምክር ቤት ሊቀመንበርነቷን ከመረከቧ አንድ ቀን አስቀድሞ፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ሰብዓዊ ቀውስን አስመልክቶ ጠንካራ መግለጫ አውጥቷል። 

  አሜሪካ በትግራይ ክልል የቀጠለው ሰብዓዊ ቀውስ በእጅጉ እንደሚያሳስባት የሚገልጸው መግለጫውበስም ያልተጠቀሱ የተለያዩ አካላት በትግራይ ክልል ሰላማዊ ዜጎችን መግደላቸውን፣ አስገድደው ማፈናቀላቸውን፣ ፆታዊ ጥቃት መፈጸማቸውንና ሌሎች ኢሰብዓዊ ጥቃት በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ ስለማድረሳቸው በተለያዩ ወገኖች ከወጡ መረጃዎች የአሜሪካ መንግሥት መረዳቱን ይገልጻል።

  የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ዕርዳታ ለማቅረብ ቁርጠኛ እንደሆነ መግለጹን የአሜሪካ መንግሥት በበጎ እንደሚመለከተው የገለጸው መግለጫውከሁሉም በፊት የኤርትራ መንግሥት ወታደሮችና የአማራ ክልል ኃይሎች ከትግራይ ክልል በፍጥነት እንዲወጡ ማድረግ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆን እንዳለበት ያሳስባል።

  ከዚሁ ጋር ተያይዞም በትግራይ ክልል እየተካሄደ ባለው ግጭት ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት ግጭቱን ለማቆም በተናጠል እንዲያውጁና በክልሉ የሰብዓዊ ዕርዳታ ሳይስተጓጎል ለማቅረብ እንዲቻል ቁርጠኝነታቸውን ማሳየት እንደሚገባቸው አሳስቧል።

  አሜሪካ አስፈላጊው የሰብዓዊ ዕርዳታ ለክልሉ እንዲቀርብ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር በጋራ ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኗን የሚገልጸው መግለጫውይኼንን መሠረት በማድረግም የአሜሪካ ተራድዶ ድርጅት የሆነው ዩኤስኤአይዲ የአደጋ ጊዜ ቡድን ሕይወት አድን ዕርዳታ ለማድረግ ወደ ክልሉ እንደሚሰማራ አስታውቋል።

  አሜሪካ በትግራይ ያለው ቀውስ እንዲያበቃ በተመድ የፀጥታ ምክር ቤትና በሌሎች የሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ አካላት አማካይነት ዕርምጃ እንዲወሰድ እንደምታደርግም አስታውቋል።

  ከዚህ አኳያም ዓለም አቀፍ የአሜሪካ አጋሮችበተለይም የአፍሪካ ኅብረትና አኅጉራዊ ተቋማት ከአሜሪካ ጎን ቆመው በትግራይ ያለው ቀውስ እንዲያበቃ የአሜሪካ መንግሥት በአብሮነት የሚሠራ መሆኑን አመልክቷል። በማጠቃለያውም የአሜሪካ መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ጋር ያለው ወዳጅነት እንዲጎለብትና ዘላቂ ሆኖ እንዲቀጥል ፅኑ አቋም እንዳለው መግለጫው አመልክቷል።

  ይህ መግለጫ ይፋ ከመደረጉ አስቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባይደን ከካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ያስታወቀ ሲሆን፣ በውይይቱ ከተነሱ አጀንዳዎች አንዱ የትግራይ ክልል ሰብዓዊ ቀውስን የተመለከተ ስለመሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ። 

  ፕሬዚዳንት ባይደን ከካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ባደረጉት ምክክር ሁለቱን አገሮች በእኩል በሚያሳስቡ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ለመተባበርና ለመሥራት የተስማሙ ሲሆንአሜሪካ ቅድሚያ በምትሰጠው የሰብዓዊ መብቶች መከበር ላይ እንደሚተባበሩም ይፋ ተደርጓል።

  ይህ ውይይት ከተጠናቀቀ በኋላም የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያ አቻቸው ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በሁለቱ አገሮች ትብብርና በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ሁኔታን በተመለከተ በስልክ መወያየታቸውን፣ የሁለቱም መንግሥታት ቃል አቀባይ መሥሪያ ቤቶች ይፋ አድርገዋል።

  በአንድ በኩል የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር ውይይት ሲያደርጉየአሜሪካ ፕሬዚዳንት ደግሞ ከኬንያ አቻቸው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር የትግራይ ክልል ሰብዓዊ ቀውስን የተመለከተ ምክክር ማድረጋቸውን የአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ባወጣው መረጃ አስታውቋል። 

  ይህ መረጃ ይፋ ከተደረገ በኋላ አሜሪካ የትግራይ ክልልን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥትን መጠየቅ እየቻለችከኬንያ ፕሬዚዳንት ጋር መወያየቷ ለምን እንደሆነ ለበርካቶች ጥያቄ የፈጠረ ሲሆንፕሬዚዳንት ባይደን ይህንን ያደረጉት መረጃ ለማግኘት ሳይሆን፣ ኬንያ በአሁኑ ወቅት አፍሪካን ወክላ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ወንበር በመያዝ እየተሳተፈች በመሆኑ ፕሬዚዳንቱ ለቀጣይ ዕርምጃቸው የኬንያን ድጋፍ ፍለጋ ያደረጉት ውይይት እንደሆነ፣ ሪፖርተር ከዲፕሎማቲክ ምንጮቹ ለማወቅ ችሏል።

  ፕሬዚዳንት በይደን የትግራይ ክልል ሰብዓዊ ቀውስን አስመልክቶ ከላይ የተገለጹትን ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ሲያደርጉበሌላ በኩል በመንግሥታቱ ድርጅት የአሜሪካ ተጠሪ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ የፀጥታ ምክር ቤት ሊቀመንበርነትን ከመረከባቸው ጥቂት ቀናት አስቀድሞ፣ ከፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል አገሮች ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል።

  አምባሰደር ግሪንፊልድ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ በተመድ የፀጥታ ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ካላቸው 14 አገሮች ተወካዮች ጋር መወያየታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። ከእነዚህም መካከል ህንድ፣ ኬንያ፣ ኢስቶኒያ፣ ሜክሲኮ፣ ኒጀር፣ ቱኒዚያና ቬትናም ይገኙበታል።

  አምባሳደሯ ባደረጉት የተመድ የፀጥታ ምክር ቤት አወቃቀር ማሻሻያን ጨምሮ ለሁም አገሮች የጋራ የሚባሉ አጀንዳዎችን አንስተው ከመምከራቸው ባለፈ፣ ከዚሁ እኩል አሜሪካ ቅድሚያ ትሰጠዋለች ያሉትን የትግራይ ከልል ሰብዓዊ ቀውስ በማንሳትም ተመካክረዋል።

  አሜሪካ ሰሞኑን ያደረገቻቸው ጥረቶች የሚጠቁሙትም ሆነ የአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ይፋዊ መግለጫ የሚያሳየው፣ የትግራይ ክልል ሰብዓዊ ቀውስን በፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ የሚሰጥበት መሆኑን ነው። 

  የጉዳዩ ወደ ፀጥታው ምክር ቤት መሄድ የሚኖረው አንድምታ 

  የአሜሪካ መንግሥትም ሆነ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተቋማት በትግራይ ክልል የተፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በዋናነት ተጠያቂ የሚያደርጉት፣ ወደ ክልሉ ገብቶ በግጭቱ እየተሳተፈ ነው ባሉት የኤርትራ ጦር ላይ ነው። 

  የአሜሪካ መንግሥት ባወጣው መግለጫምየኤርትራ ወታደሮችና የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ከትግራይ ክልል በፍጥነት እንዲወጡ ማድረግ፣ በክልሉ ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ ለማስቆም ቀዳሚው መፍትሔ እንደሆነ ጠቁሟል።

  ይህንን በፍጥነት አለማድረግ አሜሪካ በፀጥታው ምክር ቤት በኩል እንዲወሰንና እንዲወሰድ ለምትፈልገው ዕርምጃ ያጋልጣል የሚሉት ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንድ ዲፕሎማትበትግራይ ክልል ተፈጽሟል ተብሎ በተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የሚጠቀሰው የወንጀል ዓይነት የጦር ወንጀልን የተመለከተ በመሆኑ ጥቃቱን እንዲፈጸም አድርገዋል ወይም ፈጽመዋል ተብለው በሚጠረጠሩት ላይ የተለያዩ ዕግዶች ወይም ማዕቀቦች ሊጣሉ እንደሚችሉ ገልጸዋል። 

  ነገር ግን ጉዳዩ በዋናነት እያተኮረ ያለው የውጭ መንግሥት ወታደሮች ጣልቃ ገብነትንእንዲሁም ኢሰብዓዊ ጥሰቱን በመፈጸም በዋናነት የሚጠቀሰው ይኸው አካል መሆኑ ነገሩን ውስብስብ ሊያደርገውና የዚህ ውጤትም ኢትዮጵያና ኤርትራን ወደ አዲስ ጥል እንዲገቡ በር ሊከፍት እንደሚችል ሥጋታቸውን ገልጸዋል። 

  የፀጥታው ምክር ቤት የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ ክልል የገባበትን ሁኔታ ሲፈትሽ ሊነሱ የሚችሉ ጉዳዮች ውስብስብ ሊሆኑ ይችላሉ የሚሉት ባለሙያውበኢትዮጵያ በኩል የአገሪቱን ድንበር የሚጠብቀው የመከላከያ ሠራዊት በመመታቱ ድንበሩን መቆጣጠር አለመቻሉንና ለዚህ ሁኔታ የዳረገውም የሕወሓት የተሳሳተ ድርጊት መሆኑን በመጥቀስ እየወነጀለ መሆኑን ጠቅሰዋል።

  በሌላ በኩል የሕወሓት ኃይል የሮኬት ጥቃቶችን ወደ አስመራ በመተኮሱ ሉዓላዊ ደኅንነቷ አደጋ ላይ በመውደቁ የተነሳ ጦሯን ወደ ክልሉ ማዝለቋን እንደ መከራከሪያ ምክንያት ልታቀርብ እንደምትችልወይም በኢትዮጵያ መንግሥት ጥሪ ጦሯን እንዳስገባች በመግለጽ ኤርትራ ልትከራከር እንደምትችል አስረድተዋል። 

  የፀጥታው ምክር ቤት ሊወስድ የሚችለውን ዕርምጃ ለማስቀረት ሲባል በሁለቱ አገሮች መካከል በጉዳዩ ላይ ልዩነት ወይም መካካድ ከተፈጠረ፣ ሁለቱን አገሮች መልሶ ወደ ሌላ ጥል ሊከት እንደሚችል ይገልጻሉ።

  የተመድ የፀጥታ ምክር ቤት 64 መደበኛ ጉባዔ ባለፈው ሳምንት በተካሄደበት ወቅት የቀረበው አጀንዳ የኤርትራ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝን የተመለከተ ሲሆንበወቅቱም በተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የኤርትራ ልዩ ራፖርተር አብዱሰላም ባቢከር ያቀረቡት ሪፖርት ውይይት ተደርጎበታል። 

  ራፖርተሩ ኤርትራን በተመለከተ ባቀረቡት ሪፖርት፣ የኤርትራ መንግሥት ሰብዓዊ መብቶችን ለመጠበቅ ደንታ እንደሌለውና የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል ፈጽመዋል ያሉትን አቅርበዋል።

  ሪፖርታቸውን ሲያጠናቅቁም የኤርትራ ጦር በአስቸኳይ ከትግራይ ክልል መውጣት እንዳለበት ያሳሰቡት ራፖርተሩ፣ ‹‹እዚህ ላይ መነሳት ያለበት ጥያቄየኤርትራ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ የሚገኙት የኤርትራ ወታደሮች ኢሰብዓዊ ጥሰት እንዳይፈጽሙ ለመከላከል የሚያስችለው በቂ የቁጥጥር ሥልት አለው የሚለው ነው፤›› ሲሉ ጥያቄ አንስተዋል።

  የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካ መንግሥት ላወጣው መግለጫ ምላሽ የሚሰጥ መግለጫ ሰኞ ዕለት ይፋ ያደረገ ሲሆንበመግለጫውም የአሜሪካ በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ፣ በተለይም የአማራ ልዩ ኃይል በትግራይ የሕግ ማስከበር ዘመቻ እንዲሰማራ መደረጉን በተመለከተ ያወጣው መግለጫ ተገቢነት የሌለውበአንድ ሉዓላዊ አገር ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ነው ብሏል።

  ኢትዮጵያ ሉዓላዊት አገር እንደ መሆኗ የውስጥ ችግሮቿን በራሷና በመረጠችው መንገድ እንደምትፈታ የገለጸው መግለጫውይህ የማንኛውም ሉዓላዊ አገር ሥልጣን ሆኖ ሳለ የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥትን ሉዓላዊነት የሚጥስ የውጭ ኃይል ጣልቃ ገብነት ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም ብሏል።

  የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫየኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል እንዲወጡ ስለመባሉም ሆነ ስለመኖራቸው በግልጽ የሰጠው ምላሽ የለም። 

  - Advertisement -
  - Advertisement -spot_img

  ትኩስ ጽሑፎች

  ተዛማጅ ጽሑፎች

  - Advertisement -
  - Advertisement -