Friday, August 19, 2022
ሌሎች ዓምዶች

  ኢትዮጵያን አስመልክቶ ለአሜሪካ ሴኔት የቀረበው የውሳኔ ሐሳብና ሰነዱን ያመነጩት ሴናተሮች

  - Advertisement -spot_img

  በብዛት የተነበቡ

  በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ያለውን ቀውስ አስመልክቶ የፖለቲካ አቋም የተያዘበት ‹‹S.Res.97›› የሚል ቁጥር የተሰጠው የውሳኔ ሐሳብ የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ለአሜሪካ ሴኔት ቀርቦ ለዝርዝርይታ ለውጭ ጉዳይ ኮሚቴ መመረቱ የሚታወስ ሲሆን፣ የሴኔቱ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴም ረቡዕ መጋቢት 15 ቀን 2013 ዓ.ም. የመጀመሪያውን ውይይት እንደሚያካሂድ ታውቋል።

  ለሰኔቱ የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ወሓትና ሌሎች በትግራይ ክልል ግጭት ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ ኃይሎች በአሽቸኳይ ውጊያ እንዲያቆሙ፣ የክልሉነዋሪዎች ሰብዓዊ መብቶች እንዲጠብቁ፣ ያለ ምንም ዓይነት የእንቅስቃሴ ገደብ ሰብዓዊርዳታ ማድረስ የሚቻልበትን መንገድ እንዲያመቻቹና በክልሉ ተፈጽመዋል የተባሉ ሰብዓዊ ወንጀሎችን በገለልተኛ አካል ለማጣራት እንዲተባበሩ ጥሪ ለማቅረብ የተሰናዳ እንደሆነ የሚገልጽ ስያሜ ተሰጥቶታል። 

  የውሳኔሳቡ ከላይ የተጠቀሰውን ጥቅል ጭብጥና ስያሜ ይዞ የቀረበ ቢሆንምየውሳኔ ሐሳቡን ለማመንጨት መነሻ ተብለው ከተጠቀሱት መሠረታዊያን መካከል ከትግራይ ክልል ቀውስ ውጪ በኢትዮጵያ ፖለቲካ አሳሳቢ ናቸው ያሏቸውን ሌሎች ክስተቶችም ተጠቅሰዋል። 

  ከእነዚህም መካከል ኢትዮጵያ ካለፉት ቅርብ ዓመታት ወዲህ በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥስቶችና የሰብዓዊ ቀውስ ፈተናዎች እየገጠሟት መሆኑ፣ በብሔር ማንነት ላይ ያነጣጠሩ ግጭቶች፣ የማኅበረሰብ ግጭቶች፣ የተፈጥሮ አደጋና የፖለቲካ አለመረጋጋት ውስጥ ትገኛለች የሚሉት ይገኙበታል፡፡

  በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግሥት ጥቂት የማይባሉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በሰላማዊ መንገድ የመሰብስብ መብቶችን መገደቡ፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን ማሰሩ፣ ፍትሕ የማግኘት መብታቸውንም በተለያዩ አስተዳደራዊ ምክንያቶች እንዲጓተት ያደረገ መሆኑ የውሳኔ ሐሳቡን ለማመንጨት መነሻ ናቸው ከተባሉ አሳሳቢ ምክንያቶች መካከል ተጠቅሰዋል።

  ከትግራይ ክልል ቀውስና በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች በየጊዜው ከሚነሱ የብሔር ግጭቶች፣ የፖለቲካና ሰብዓዊ መብቶች ላይ ከሚደረጉ አፈናዎች በተጨማሪ፣ ኢትዮጵያ በምትገኝበት ቀጣና የሚስተዋሉ አሉታዊ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችም በአሳሳቢነት ተጠቅሰዋል።

  የትግራይ ክልል ግጭት በውስብስብ በሆኑ ቀጣናዊና ዓለም አቀፉዊ ሁነቶች ውስጥ የተፈጠረ መሆኑ፣ ከእነዚህም መካከል ታላቁ የህደሴ ግድብን አስመልክቶ በኢትዮጵያ፣ግብፅናሱዳን መካከል ያለው ልዩነት ያልተፈታ መሆኑ፣ በኢትዮጵያናኤርትራ መካከል የተፈጠረው የሰላም ስምምነት፣ በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው አልሸባብ የደቀነው የደኅንነትጋት ባለበት፣ ዓለም አቀፋዊና ቀጣናዊ ኃይሎች ኢትዮጵያ ባለችበት አካባቢ የፖለቲካ የበላይነት ለመያዝ ከፍተኛ ትግል እያደረጉ መሆናቸው፣ በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል የተፈጠረው አሳሳቢ የድንበር ግጥጭትና ሱዳን አቅሙ ባልጠናሞክራሲ ውስጥ የመንግሥት ሽግግር እያደረገች የምትገኝ መሆኗ በአሳሳቢነት የቀረቡ ውጫዊ ምክንያቶች ናቸው ተብሏል። 

  ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ፖለቲካዊ ፍጥጫዎች ኢትዮጵያ የምትገኝበትን ቀጣና በከበቡበት ወቅት፣ ከመቶ ሚሊዮን በላይዝብ ያላት ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ቀውስናሌሎች ውስጣዊ ፖለቲካዊ ቀውሶች ውስጥ መግቧቷ ለኢትዮጵያም ሆነ ለዓለም ሰላም አሥጊ በመሆኑ፣ የውሳኔ ሐሳቡ በአሜሪካ ሴኔት እንዲፀድቅ መቅረቡን የውሳኔሳቡ ያስረዳል። 

  ይህንንም መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥትን ጨምሮ፣ ኤርትራና ሕወሓት፣ እንዲሁም የአሜሪካ መንግሥት ሊያደርጉ ይገባቸዋል ያላቸውን ሰባት ነጥቦች የውሳኔ ሐሳብ አሥፍሯል።

  መዘርዝሮችን አካቶ በቀረበው ባለሰባት ነጥብ የውሳኔ ሐሳብ ውስጥ ከመጀመሪያው እስከ አምስተኛው ነጥብ ድረስ የተዘረዘሩት ክሰተቶቹን ለማውገዝ፣ ሥጋትንና አድናቆትን ለመግለጽ ጥቅም ላይ ውለዋል።

  በዚህም መሠረት የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ መንግሥትና በሕወሓት መካከል የተፈጠረው ፖለቲካዊ መካረር ወደ ግጭት መቀየሩ ተገቢ እንዳልነበር በመጥቀስ፣ በግጭቱ ወቅትም ሆነ ግጭቱን ተከትሎ በሰቪሎች ላይ የተፈጸሙ ጥሰቶችን እንደሚያወግዝ ያስታውቃል። 

  የሱዳን መንግሥት ከትግራይ የተፈናቀሉ ስደተኞችን መቀበሉን በማድነቅ፣ የኤርትራ ጦር ከትግራይ ክልል እንዲወጣ ይጠይቃል። በትግራይ ክልል የተቋረጡ መሠረታዊ አገልግሎቶች በአስቸኳይ ተጠግነው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ በመጠየቅ የመጀመሪያዎቹን አራት ነጥቦች ያጠናቅቃል። 

  በተራ ቁጥር ስድስት ደግሞ በትግራይ ክልል ግጭት እየተሳተፉ የሚገኙ በሙሉ በፍጥነት ግጭቱን እንዲያቆሙ የሚጠይቅ ሲሆን፣ ለሰብዓዊርዳታ አቅርቦት ያልተገደበ እንቅስቃሴ እንዲፈቅዱና በግጭቱ የተፈጸሙ ኢሰብዓዊ ጥሰቶች በገለልተኛ አካል እንዲጣሩ ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀርባል። 

  የውሳኔ ሐሳቡ በሴኔቱ የሚፀድቅ ከሆነ በቀጣይ ፖለቲካዊ አንድምታ የሚኖራቸው የውሳኔ ሐሳቡ ክፍሎች፣ በተራ ቁጥር አምስትና ሰባት ላይ የተጠቀሱት ናቸው።

  በተራ ቁጥር አምስት ሥር ለኢትዮጵያ መንግሥት የቀረበ ጥሪ የተቀመጠ ሲሆን፣ በዚህም የኢትዮጵያ መንግሥት የሕወሓት አባላትን በቁጥጥር ለማዋል የሚያደርገውን ጥረት በተቻለ መጠን በዝቅተኛ የኃይልርምጃ መከናወን እንደሚገባውና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የሕወሓት አባላት አያያዝም የኢትዮጵያንናዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ሕጎችን ባከበረ መንገድ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት ይላል፡፡

  በዚሁ ተራ ቁጥር አምስት ሥር ለኢትዮጵያ መንግሥት የቀረበው ጥሪ በፖለቲካ እንቅስቃሴያቸው ምክንያት የታሰሩ የተቃዋሚ ፖለቲካ አመራሮችን እንዲፈታ፣ በተመሳሳይ በዘገባቸው ምክንያት የታሰሩ ጋዜጠኞችን እንዲለቅ፣ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሰብዓዊ መብቶችን ጨምሮ የመናገርና በፖለቲካ የመሳተፍ መብቶቻቸውን፣ በብሔራቸው፣ በፖለቲካ አቋማቸውና ለገዥው ፓርቲ ባላቸው ቅርበት መድልኦ ሳያደርግ እንዲያከብር ጥሪ አቅርቧል። 

  በተጨማሪም በኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለመትከልና ወደሞክራሲ የሚደረገውን ሽግግር የተቃና ለማድረግ ሁሉም ወገን የሚሳተፍበት የብሔራዊ መግባባት ውይይት እንዲኖር፣ ግጭቶች በዘላቂነት እንዲፈቱ ለማስቻል መንገዱን መጥረግ አለበት የሚል ጥሪ አቅርቧል።

  በተራ ቁጥር ሰባት ሥር የተቀመጠውውሳኔ ሐሳብ የአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት፣ የገንዘብ ግምጃ ቤትና የአሜሪካ ተራድኦ ተቋም ዩኤስኤአይዲ የቀረበ ነው፡፡ እነዚህ ተቋማት ከኢትዮጵያና ከኤርትራ መንግሥት እንዲሁም ከሕወሓት አመራሮች ጋር በመነጋገር በትግራይ ያለው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም የማመቻቸት ሥራ እንዲያከናውኑ ጥሪ አቅርቧል።

  በተመሳሳይ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የሚሳተፉበት የብሔራዊ መግባባት ውይይት የሚመቻችበት ሁኔታ እንዲፈጠር እንዲያግዙ፣ ከተቋረጠው የአሜሪካ ዕርዳታ ውስጥ ሕይወት ለማዳን የሚውል ዕርዳታ ለኢትዮጵያ የሚቀርብበትን መንገድና መሥፈርት እንዲቀርፁና ሰብዓዊ ዕርዳታ እይዲያቀርቡ ጥሪ አቅርቧል። 

  በትግራይ ግጭት የተፈጸሙ ኢሰብዓዊ ጥሰቶች በገለልተኛ ወገን እንዲጣሩና ተፈጽመዋል ተብለው የሚቀርቡ ሪፖርቶች ከተረጋገጡም፣ ጥሰቱን በፈጸሙት ላይ ጥብቅ የሆነ ተጠያቂነት መውደቁን እንዲያረጋግጡ ጥሪ ያቀርባል።

  በተጨማሪም በኢትዮጵያ በመንግሥትም ሆነመንግሥት ባልሆኑ የታጠቁ ኃይሎች፣ ብሔር ተኮር ግጭትና መሰል ሰፊ ወንጀል ዳግም እንዳይከሰት ለመከላከል የሚያስችሉ ዲፕሎማሲያዊ ተግባራትን እንዲያከናውኑ ጥሪ ያቀርባል።

  በማጠቃለያውም የትግራይ ክልል ግጭት እንዲፈታ ከሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር እንዲተባበሩ፣ ግጭቱ የፀጥታው ምክር ቤትን ጨምሮለም አቀፋዊ ትኩረት እንዲያገኝ እንዲጥሩ ጥሪውን አቅርቧል። 

  የውሳኔ ሐሳቡን ያመነጩት የአሜሪካው ሴናተር ጀምስ ራይች፣ እንዲሁም ሰሞኑን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባይደን ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ወደ ኢትዮጵያ የተላኩት ሴናተር ክሪስ ኩንስ ናቸው። 

  ሴናተር ክሪስ ኩንስ ሰሞኑን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር የተገናኙ መሆናቸው ይታወሳል። 

  በውይይታቸው ወቅትም በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት በተመለከተ፣ ከመነሻው አንስቶ አሁን እስካለበት ድረስ ያለውን ሁኔታ አቶ ደመቀ ያስረዱ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። 

  በዚህ ወቅትም ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይዋ የውጭ አገሮችን ጣልቃ ገብነት ፈጽማ እንደማትፈቅድ እንደተገለጸላቸው፣ በተለይም የአሜሪካ መንግሥት የአማራ ክልል ኃይል ከትግራይ ክልል ለቆ እንዲወጣ በማለት ያወጣው መግለጫ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጋፋ ስለመሆኑ እንደተነገራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።

  የውሳኔሳቡን ካመነጩት ሴናተር ጀምስ ራይች በተጨማሪ ሌሎች አሥራ አንድ ሴናተሮች የውሳኔሳቡን ደግፈው ፈርመውበታል። 

  የውሳኔሳቡን ከደገፉት ሴናተሮች በተጨማሪየውሳኔሳቡን በዝርዝር እንዲመረምር የተመራለት የሴኔቱ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ሰብሳቢ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ በተደጋጋሚ ጊዜ ሥጋታቸውን በመግለጽ የሚታወቁ ናቸው። 

  በዚህም ምክንያት የውሳኔ ሐሳቡ የመፅደቅ ዕድሉ ከፍ ያለ ቢሆንም የውሳኔ ሐሳቡ የአሜሪካ መንግሥት የፖለቲካ አቋም መግለጫ ብቻ እንደሚሆን፣ ነገር ግን ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ፖለቲካዊ ሁነቶችን መሠረት በማድረግ ከፍ ያለ ዕርምጃ በኢትዮጵያ ላይ ለመውሰድ አሜሪካ ልትጠቀምበት ትችላለች እየተባለ ነው። 

  - Advertisement -
  - Advertisement -spot_img

  ትኩስ ጽሑፎች

  ተዛማጅ ጽሑፎች

  - Advertisement -
  - Advertisement -