Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናምርጫ በሐዋሳ

  ምርጫ በሐዋሳ

  ቀን:

  ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ በሐዋሳ ከተማ እየተካሄደ ሲሆን፣ የምርጫ ጣቢያዎች ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ክፍት ሆነዋል፡፡ ሪፖርተር በከተማው ለድምፅ መስጫ የተዘጋጁትን የምርጫ ጣቢያዎች ተዟዙሮ ተመልክቷል፡፡
  በበርካታ ጣቢያዎች መራጮች በጠዋት ተነስተው ድምፅ መስጠታቸውን ለመታዘብ ተችሏል፡፡ 
  በከተማዋ ጉዱ ማሌ -5 (Gudu Malle-5) ፒያሳ ወፍጮ ሠፈር ጣቢያ፣ መናኸሪያ የምርጫ ጣቢያ አካባቢዎች ሪፖርተር ያነጋገራቸው የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ምርጫው በሰላም እየተካሄደ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ በምርጫ ቁሳቁስ በኩልም ችግር እንዳላጋጠማቸው ገልጸዋል፡፡ 
  በምርጫው  ውድድር ተካፋይ የሆኑትን የብልፅግና፣ መኢአድ፣ እንዲሁም የኢዜማን ተወካዮች ይህንኑ ለሪፖርተር አረጋግጠዋል፡፡ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ተወካዮችም እስካሁኑ የምርጫ ሒደት እስከ ረፋዱ ድረስ ምንም ችግር እንዳላጋጠማቸው አመልክተዋል፡፡
  የሲዳማ ክልል ባለሥልጣናት ርዕሰ መስተዳድሩን አቶ ደስታ ሌንዳሞን ጨምሮ፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ጥራቱ በየነን ጨምሮ በሐዋሳ ከተማ የተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ ሰጥተዋል፡፡ ባለሥልጣናቱም ከድምፅ መስጠቱ በኋላ የችግኝ ተከላ ማካሄዳቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...