Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየኬብል ስርቆት በፈጸሙ ግለሰቦች ላይ እስከ 12 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ተወሰነ

  የኬብል ስርቆት በፈጸሙ ግለሰቦች ላይ እስከ 12 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ተወሰነ

  ቀን:

  የአዳማ ከተማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኢትዮ ቴሌኮም ኮፐር ኬብሎችን በቆረጡና ስርቆት በፈጸሙ ሦስት ግለሰቦች ላይ፣ እስከ 12 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት መወሰኑ ተገለጸ፡፡

  ለጋሳ ኃይሉና ፉአድ አሚንን የተባሉት ተከሳሾች በአዳማ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ የኢትዮ ቴሌኮም ንብረት የሆኑ ኮፐር ኬብሎችን በመቆራረጥ ይዘው ለመሰወር ሲሞክሩ፣ በአካባቢው የፀጥታ ኃይሎች እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ኢትዮ ቴሌኮም ለሪፖርተር በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

  አቃቤ ሕግ በአዳማ ከተማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ የመሠረተባቸው ሲሆን፣ ታኅሳስ 5 ቀን 2014 ዓ.ም. የዋለው ችሎት አንደኛ ተከሳሽ ለጋሳ ኃይሉ ላይ የ11 ዓመት ፅኑ እስራት ሲወስን፣ ሁለተኛ ተከሳሽ ፉኣድ አሚንን ደግሞ በ12 ዓመት ፅኑ እስራት ቀጥቷል፡፡

  ሦስተኛው ተከሳሽ አብዱልፈታ ከድርም እንዲሁ በአዳማ ከተማ ጎሮ ቀበሌ ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ኮፐር ኬብሎችን ሰርቆ ሲሄድ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል፡፡ ዓቃቤ ሕግም በአዳማ ከተማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ በመመሥረቱም ታኅሳስ 5 ቀን 2014 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ተከሳሹ በሰባት ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

  ሪፖርተር ያነጋገራቸው የኢትዮ ቴሌኮም ዋና የኮሙዩኒኬሽን መኮንን አቶ መሳይ መኮንን፣ የኮፐር ኬብሎች በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ አገር ውስጥ እንደሚገቡ ገልጸው በውስጡ የሚገኘውን ኮፐር አቅልጦ ለመጠቀም ሲባል በተደጋጋሚ ስርቆት እንደሚፈጸም አስረድተዋል፡፡

  እንደ አቶ በመሳይ ገለጻ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ወንጀል ሲከሰሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ሲወሰንባቸው የነበረው እስር ከአንድና ከሁለት ዓመት የሚዘል አይደለም፡፡ አመክሮ ተሰጥቷቸው በወራት ውስጥ የሚፈቱና በዋስ ወጥተው የፍርድ ሒደታቸው የሚጓተት ተከሳሾች እንዳሉም አክለዋል፡፡

  ኢትዮ ቴሌኮምም ‹‹ጠንካራና የማያዳግም›› ዕርምጃ እንዲወሰድ ከሕግ አካላት ጋር ንግግር እያደረገ መሆኑን ጠቁመው፣ አሁን የተላለፉት ውሳኔዎች ከዚህ በፊቶቹ አንፃር ‹‹ትልቅ›› የሚባሉ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...