Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየፈጠራ ሐሳብ ያላቸው በመንግሥት ዋስትና ብድር የሚያገኙበት ስትራቴጂ መዘጋጀቱ ተነገረ

  የፈጠራ ሐሳብ ያላቸው በመንግሥት ዋስትና ብድር የሚያገኙበት ስትራቴጂ መዘጋጀቱ ተነገረ

  ቀን:

  የፈጠራ ሐሳብ ያላቸው በመንግሥት ዋስትና ብድር የሚያገኙበትን አራር ለመዘርጋት ያስችላል የተባለ ስትራቴጂ መዘጋጀቱንራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ።

  ስትራቴጂው ከዩኒቨርሲቲ የተመረቁም ሆ የፈጠራ ሐሳብ ያላቸው ሌሎች ግለሰቦች ወደ ቢዝነስ መቀየር የሚችል ሐሳብ ሲኖራቸው መንግሥት ዋስ በመሆን በብድር መልክ ገንዘብ እንዲያገኙ የሚደረግበት መሆኑንራና ክህሎት ሚኒስቴር የፖሊሲና ስትራቴጂ ጥናትና ምክትል ዳይሬክተር አቶ በዛርቅ ከተማ ገልጸዋል።

  መንግሥት የሚገባው ዋስትና ‹‹ሙሉ ለሙሉ›› ወይም ‹‹በከፊል›› ይሁን የሚለው እስካሁን ውሳኔ አለማግኘቱን ገልጸው በሚቀጥሉት ስት ወራት ውስጥ የፈጠራ ሳቡ ባለቤቶች የሚሸፍኑት መጠንና ከመንግሥት የሚጠበቀው የዋስትና መጠን ይወሰናል ብለዋል።

  ከተለያዩ ብድር አቅራቢዎች ጋር በጋራ በመሆን የሚዘጋጀው ብድር የፈጠራ ሐሳብ አዋነቱ ተገምግሞ የሚሰጥ ሲሆን በረም ጊዜ የሚመለስና ለሌሎች የሚተላለፍ መሆኑን አቶ በዛወርቅ አስረድተዋል፡፡

  ብድሩ ያለ ማስያዣ የሚቀርብ በመሆኑ ተበዳሪዎቹ የሚኖራቸውን ተዓማኒነትና የመራት አቅም ለመፈተሽ ፈተና ወስደው ሲያልፉ ብቻ የሚሰ እንደሆነም አክለዋል። ይህም ከዚህ ቀደም በተለያ ጊዜያት ለወጣቶች በተሰጠው ተዘዋዋሪ ፈንድ ላይ ያጋጠመውን ያለ መመለስ ችግር እንደሚቀርፍ ይጠበቃል ብለዋል።

  ስትራቴጂው ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተደርጎበትና በዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ድቆ በ2015 ዓ.ም. ወደ ተግባር ይገባል ተብሎ እንደሚጠበቅ አብራርተዋል።

    በሌላ በኩል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚገጥማቸውን የገንዘብ ችግር ለመቅረፍ እንዲቻል የጥቃቅንና አነስተኛ ባንክ ለማቋቋም ጥናት እየተደረገ መሆኑን አቶ በዛወርቅ ተናግረዋል።

  ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ተብለው በሦስት ዘርፍ የተከፈሉት ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የመሪያ ካፒታላቸው ከ200,000 ሺ ብር እስከ ስት ሚሊን ብር ሲሆን፣ በተለይ መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እስከ 45 ሚሊን ብር ብድር እንዲያገኙ የሚያስችል እንደሚሆን ይጠበቃል።

  በተለያየ መንገድ ብድር የሚቀርብ ቢሆንም ኢንተርፕራይዞቹ በቂ ማስያዣ ማቅረብ የማይችሉ በመሆናቸው የሚፈልጉትን ብድር ማግአለመቻላቸውን የገለጹት አቶ በዛወርቅ የጥቃቅንና አነስተኛ ባንክ ሲቋቋም ያለ ማስያዣ ብድር ማግኘት ይችላሉ ብለዋል።

  ከብድር የገንዘብ አቅርቦት የሚያገኙ ኢንተርፕራይዞች ከ15 በመቶ እንደማይበልጡ የሚገውም ገንዘብ ከፍተኛ የወለድ ምጣኔ የሚታሰብበት በመሆኑ በጊዜው ለመመለስም እንደሚቸገሩ አስተዋል።

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት አልፈጸምኩም አለ

  የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ...

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...