Monday, August 8, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ልናገርክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ጆሮዎን ጣል ዓይንዎን ከፈት ያድርጉ

  ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ጆሮዎን ጣል ዓይንዎን ከፈት ያድርጉ

  ቀን:

  ሰላም ለስዎና ለሚወዱት ሁሉ ይሁንለኢትዮጵያም ሰላምና ብልፅግናን ያድልልን፡፡ ህንን ማስታወሻ ስጽፍልዎት እደሚደርስዎት በመተማመን ነው፡፡ ለበላይ አስተያየት መስጠት በጎን ከማማት የተሻለ ነው ብዬ ስለማምንየተቻለኝን ምክረ ሳብ ለማቅረብ እክራለሁ፡፡ እኔ ባለሁበት አገር የወገን አስተያየት የተከበረና የተመገነ ነው፡፡ በአገራችን የተለመደ ወይስ አዲስ ነገር? ስል ራሴን ጠይቄ ለመልካም አስተያየት ችግር አይኖርም በማለት በረታታሁና እንደሚከተለው ምክሬን ለመለገስ ተነሳሳሁ፡፡ ህንንም ስተያየት ለመጻፍ የተነሳሳሁበት ዋናው ምክያት ለውድ ገሬ ያለኝን ፍቅርና ግዴዬን ለመወጣት እንጂ ሌላ ምንም የምሻው ነገር እንደሌለኝ ላረጋግጥ እወዳለሁ፡፡

  ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በሚያደርጉትና በሚሞክሩት ገር ማሻሻል ርምጃዎ እጅግ ደስ ይለኛል እደግፍዎታለሁም፡፡ አገራችን መከራና ችግር ተደራርቦ በገጠማት በዚህ ዘመን የሁላችን ብረት እንደሚያስፈልግዎ ሁላችንም እንገነዘባለን፡፡ በበኩሌ በመገንዘብም ብቻ ሳይሆን የድርሻንም ለመወጣት የተቻለኝን እያደ ነው፡፡ የበለጠ ለማድረግም ዝግጁ ነኝ፡፡ ይሁን እንጂ ስህተት መስሎ ለሚታየኝ ጉዳይ አስተያየት ከመስጠት ልቆጠብም፡፡ በምሰጥዎት አስተያየት ይህንን አታሳጣኝ ይበሉ እንጂ ቅር እንዳይሰኙ አደራ ለማለት እሻለሁ፡፡                                                                                                                                

  ምዕራባያን በኩል ያጋጠዎትን ማለብኝነት ገትረው በመቋቋምዎ ዓለም አድንቆዎት ነበር፡፡ ኢትዮጵያያንም ዳር እስከ ከዳር በአገር ቤትም በውጪም ከጎንዎ እደተለፉ በናት ሳይተ፡፡ በአሜሪካና በአውሮ በረዶ ውርጭና ቆፈን ሳይበግራቸው ብዙ ማይሎችን በእግር ተጉዘው ያሳዩትን ቆራጥነትና ያመጡትንም ውጤት እርስዎም እንደሚገነዘቡ አምናለሁ፡፡ በመከለኛው ምራቅና በአፍሪካም ሙቀቱንየአገሩን ገዥ ግልምጫ ቁጣና መሰል ችግሮች ተቋቁመው ያሳለፉትን መገንዘብና ለምን ይህ ሁሉ ሆነ ብለው የማስተዋሉን ጉዳይ ለክቡርነት መንገር ለአንበ መምተር እንዳይሆንብኝ ስል ሳቤን እዚህ ላይ እገታለሁ፡፡

  ይሁንና ዛሬ የምንመለከተው የፖቲካ ሩጫ አገርን የሚጠቅም ሳይሆን ገርን የሚያጠፋ ነውና ጥንቃቄ ይደረግበት፡፡ ኢትዮጵያ በ1923 ዓ.. ንጉ ነገሥ አፄ ኃይለ ሥላሴ የቀዳሚውን የአፄ ምኒልክ ፋና ተከትለው ያደረጉት የልማት ርምጃ እንዴት ነበር? ስንት ትምህርት ቤቶች ነበሩ? ስንት ሆስፒታሎች ነበሩ? ሁለት ትምህርት ቤቶች የምኒልክና የተፈሪ መኮንን ብቻ ልነበሩምን? ታዲያ ንጉእነዚህ ተነስተው ንደኛ ደረጃዎች ሁለተኛ ደረጃዎችና ኮሌጆችን ሠርተው ዛሬ ለዚህ ውጥንቅጥ ገሪቱን ያዳረውን ትውልድ ስተምረው አብቅተው ነበር፡፡ ነገር ግን በተማርነው ገራችንን ከመርዳትና ከማልማት ይልቅ የግል ጥቅማችንን በመሻት ሊያጠፉን ኮብኩበው ለሚጠብቁን ዋና መሣሪያ በመሆን እነሆ ለዚህ የርስ በርስ መጠፋፋት ደረስን፡፡

  እያልን እያልን በ1960ቹ የመጣው ለውጥ አሻሽሎን ሄደ ወይስ አጥፍቶን? ባለፉት 40 ዓመታት ውስጥ የነበረው ለውጥ በቀደምት ዓመታት ውስጥ የተቋቋሙትን ተካ ወይስ አጥፍቶ ጠፋ? ብሎ ማመከሩና ነባሩን ከማጥፋት አሻሽሎ መሄድን ያሳየን ይሆናልና ይህንን ማመዛዘኑ መልካም ስለሚሆን ይታሰብበት፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አስበውም  ከመንግሥቱ ኃይለ ማርያምና ከመለስ ዜና በተሻለ እያራመዱ በመታየትዎ ደስ ብሎኛል፡፡ ነገር ግን የበሰሉና ልምድ ያካበቱ አማካሪዎች ቢኖሩዎት ጥሩ ነው፡፡ በዚህ ዘመን ዕድሜያቸው 30 ሳይሞላ ተምረው ዶክተር የሆኑ ገና ሮጠው ያልጠገቡ የኑሮን ጣዕም ያላጣጣሙ፣ በትምህርታቸው ተገቢውን ፈጽመው ገና ልምድ የሚሹትን ሁሉ የቁንጅና ውድድር ይመስል ወደ ከፍተኛ ሥልጣን ማለፉ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንዳይብስ ይጠንቀቁ ለማለት እወዳለሁ፡፡

  በርግጥ በአሜሪካ በሥራ ላይ ልምድ (On Job Training) በሚሉት አሠራር በሥራ ልምድ አካብተው ለትልቅ ደረጃ የሚደርሱ አሉ፡፡ ታዲያ እነዚህ ሚኒስትርነትና ሚኒስትር ኤታነት በዚያ ደረጃ ሲታጩ አይታወቅም፡፡ ዛሬ ታላቅ ተብላ ሁሉን ሰባሰ በዚያውም ለግል ጥቅሟ ሌላውን ምታፋጅ አሜሪካ፣ ከሌላው አገር ቀምተው ሁሉን አሰባስበው ልማት እንጂ ወሰን ዬና ቀበሌ ሳይሉ 360 ሚሊዮን ሕዝብ ይኖርባታል፡፡ አሜሪካ ከዓለም በሙሉ የመጣውን ስታስተናግድየተስተናገደውም ዜጋ ነ ለማለት የሚኩራራበትን ሁኔታ ስንመለከት እኛ ምን እየሆንን ነው? የሚያሰኝ ጥያቄ ያጭርብኛል፡፡ ኦሮሞ ማራ ትግሬ ሆኗል ዘፈኑ፡፡ ጉራጌው ሐዲያው ወላይታው ሲዳማው ከፋው ኩሎው ኮንታው ሚራው ናኦው፣ ቤኔሾው አርጎባው ኧረ ስንቱ? ታዲያ ይህ ሁሉ በወሰንና በዬ ከተከፋፈለ ማነው ባላገሩ? መፍትሔውስ ምን ሊሆን ነው? ይታሰብበት፡፡                 

  ይህንን የማይበጅ ልም ወይም ቅዤት ትቶ ሁሉም በኢትዮጵያዊነት አብሮና ተባብሮ ለልማት እንዲነሳሳ ማድረግ ይገባል፡፡ ተቀራርቦና ተዋህዶ በአንድነት የሚሻሻልበት መንገድ ቢቀየስ መልካም ነው፡፡ እርጋታ በተላበሱ፣ በማያወላውሉ ወገንተኛ ባልሆኑ ምሁራን ተንቶ የረጋች ታሪኳን የጠበቀች አገር ክብርና መብቱን የሚያውቅ ትውልድ መስመር እንዲይዝ ቢደረግ ይበጃል፡፡ የራሱንና የወገኑን ክብር የሚያስጠብቅ ትውልድ የወሰደውን ያህል ጊዜ ወስዶ ለአንድ ወገን ሳይሆን ለመላው ኅብረተሰቡ እንዲያገለግል መቅረፅ የማይታለፍ የቤት ሥራ መሆን አለበት፡፡ ይህንን አኩሪ ሥራ መቀየስና በማስጀመር አሻራዎን ለታሪክ ጥለው ቢያልፉ አፄ ቴዎድሮስ ምናልባትም አፄ ምኒልክ (ይውደዱዋቸው ወይም አይውደዱዋቸው አላውቅም) ተርታ ለመሠለፍ ቢሞክሩ መልካም ስል አሳስብዎታለሁ፡፡

  ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በአገራችን እንደ ዛሬ ስብጥርጥሩ ሳይበዛና ሳንራኮት በአንድ ቋንቋ ሁሉም ሕዝብ ተግባብቶ ይኖር ነበር፡፡ ክቡር አቶ ይልማ ለንጉሠ ነገቱ እንዲህ ሲሉ ሳብ አቅርበው ነበር፡፡ አማኛ ሲባል የአንድ ጎና ሁሉን ንድ የማያደርግ ስለሚመስል አማኛ ከማለት ኢትዮጵያዊኛ ብንል ሁሉን ያካትታል አሉ፡፡ ሐሳቡንም ንጉሡ ተቀብለው ሥራ ላይ የሚውልበትን መንገድ እንዲያጠኑ ትወደድ ዘውዴ ገብረ ሕይወትን ከንቲባ ሐረጎትን በማካተት ቶ ይልማን በሊቀመንበርነት ማጀር ጄኔራል በበ ገመዳን፣ ሌተና ጄኔራል ከበደ ገብሬን ሜጀር ጄኔራል ይልማ ሺበሺንና ሌሎችም ነበሩበት በአባልነት በማድረግ ሥራ ላይ ሊውል ሲታሰብ ደርግ የተባለ ተውሳክ ደርሶ ሁሉንም ነገር ፈረሰ፡፡                                                                                      

  አፍሪካያውያን የገዛ ቋንቋቸው ጠፍቶባቸው መልሰው ለመማር ባለመቻላቸው፣ ከሥልጣኔ ወደ ኋላ ላለመቅረት ሲሉለመዱትኝ ገዥዎች ቋንቋ ቀጥለው እነሆ በዚያው ረግተው አገራቸውን ይመራሉ፡፡ ቋንቋ መገናኛ እንጂ የማንም አይደለምና፡፡                                                                                                  በኛ አገር የተረሳው ነገር የቤተ ክህነት ትምህርት ባይኖር ነፍጠኛው ጠላትን ተከላክሎና ድንበር አስጠብቆ ነፃነትን ባያስረክበ ሮ ዛሬ የምንፈናከትበት መለያየት ይኖር ነበር? ወይስ የፈረንጅ ባሪያ ሆነን እንቀር ነበር? ብለን በማሰብ ሕዝባችን ወደ ልቦናው ተመልሶ ስለአገሩ መልካምነት በማሰብ ለልማት እንደሚሽቀዳደም ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡ እርስዎም ይበርቱ የኢትዮጵያ እምላክ ይርዳዎት፡፡

  በመልካም አንደበትዎና በማራ አቀራረብዎ ወቃሾንም ሆነ ደጋፊዎን በማግባባት አስደስተው ይሸኛሉ፡፡ ይህ ደግሞ ዘላቂነት ውጤታማ ለመሆን ሳይሆን ጊዜያዊ ማቀዝቀዣ ነው የሚሆነው፡፡ ከልብዎ አዋቂዎችን አማክረው ተገቢውን ቢሠሩ መልካም ይሆናል፡፡ እዚህ ላይ የግብፅ መሪ የነበሩት ማል አብዱልናስር ትዝ ሉኝ፡፡ የግብፅን ሕዝብ ጉም ሲያስጨብጡ ቆዩና በስድስቱ ቀናት ጦርነት ሲሸነፉ ልጣኔን እለቃለሁ አሉ፡፡ቡም በዚህ በቀውጢ ጊዜ እንዴት ትለቃለህ አብረንህ እንሞታለን ቢልም፣ እሳቸው ግን ተሸነፉ እስከ ዛሬም እንደ ተሸነፉ ነው፡፡

  ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የእርስዎ ኃላፊነት ለመላው ኢትዮጵያዊያን መሆኑን ሁሌም ስለሚገልጹ ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ የለኝም፡፡ ግን እንዳንዴ መስመር የለቀቁ ነገሮች ይታያሉ፡፡ እነዚህ ደግሞ ምን ይሆኑ ብለው ጠይቁኝ በአገር ደረጃ ተነግሮ የሰዎች አስተያየት ታክሎበት ሁኔታው ምን ያስከትል ይሆን? ተብሎ ተንቶ የሚመለከታቸው አካላት ተሰባስበው መወሰንና የሁሉንም አዎንታ ማግኘት ሲገባዎ ሁሉንም ነገር በግልዎ የሚወስኑ ይመስላል፡፡ ይህ ደግሞ እርስዎመጨረሻ የማያምር ሊሆን ስለሚችል ቢያስቡበት የተሻለ ይሆናል፡፡ በሕዝብ የተመረጠ መሪ ለተወሰነ ዘመን ስለሚሠራ በራሱ ፍላጎት የአገርን ርማ ይለውጥም፡፡ እነ መለስ የተጠሉበት ዋናው ምክያት እንደ ፈለጋቸው ስለፈጩ ነው፡፡ ቢሆንም ሰንደቅ ዓላማችንን መልኳን በተጨማሪ ኮከብ ሊበርዟት በእጅ አዙር ሲያስነሩና ሲያስፈራሩ ቆይተው ነው የለወጡት፡ እርስዎ ግን ኮክ በዋናው ደባባይ ላይ ርማ አድርገው ሲያስቀምጡ ዱብ ዕዳ ነበር፡፡  ይህ ለምን ሆነ ብሎ ለመጠየቅ ሕዝቡ የሚጠይቅበት ደባባይ የለም ደባባዩ ክቡርነትዎ ብቻ መሆንዎ ነው፡፡                                       

  እንዲህ ዓይነት አነስተኛ ስህትቶች መታረም የሚገባቸው ናቸውና ለምን ከሚወድዎት ሕዝብ ጋር ሆድ ይባባሳሉ? ገና ብዙ ዘመን ያዎት ወጣት የኢትዮጵያ ተስፋ የሚሆኑ ሰው ባልታሰባልተጠበ ሰዓታት ውስጥ አንዳንድ ያልታሰቡና ያልተጠበቁ ነሮችን በድንገት ጣል እያደረጉ ደጋፊዎችዎን ያስደነጣሉ በዚህም ጉዳይ በጣም ያስቡበት፡፡ መሪ በመሪነቱ የሚመነውም ሆነ የሚጠላው ውሎ አድሮም ከሕዝቡ የሚራራቀው ባልተጠበቀና ባልታሰበ ሁኔታ ስለሆነ ያስቡበት፡፡ እርስዎ ወደ ሕዝብ ጆሮ የተነፈሱት ሁሉ በሚደርስበት በዚህ ዘመን ዕድሉን አግኝተዋል፡፡ የፈለጉትን የሚያዝዙበትና የሚያገኙበት ዘመንም ነው፡፡ በታደሉት መልካም ንደበትና አቀራረብ ጊዜዎን ይጠቀሙበት የሕዝብን ፍቅር ይሸምቱ፡፡

  በአ ምኒልክ ዘመን መገናኛውም ወሬውም የተፋጠነና የተራቀቀ አልነበረም፡፡ ታዲያ አ ምኒልክ ከዘመናቸው የቀደሙና የለጠኑ ታላቅ መሪ ስለነበሩ አንድን ሰው ከመሾማቸው በፊት ሕዝብ ምን ይል ይሆን? ብለው ሰላዮቻቸውን በየመንደሩ ይልካሉ፡፡ እቶ እገሌ ሊሾም ነው የሚል መረጃ አስነግረው ወሬው እንዲናፈስ ይደረጋል፡፡ በዚህ መሠረት የሕዝቡ አስተያየት ከደረሳቸውና ሁኔታውን ከተረዱ በኋላ እንደ አስተያየቱ ሹመቱ ይድቃል ወይም ይቀራል፡፡ እርስዎ ግን የሕዝቡን አስተያየትም ሆነ መቀበሉን ሳያረጋግጡ ወጣቱን ያስደሰቱ እየመሰዎት ትናንትን ያላዩ ለነም ለማሰብ ተክሮ የሌላቸውን ሰባስበው ታላላቅ ኃላፊነት ይሰጣሉ፡፡ የወጣቱን ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ ከአንድ ታላቅ አስተዳዳሪ የማይጠበቅ የችኮላ ሥራ የሚሠሩ ስለሚመስል፣ ይህ አሠራር ቢስተካከልና ሥርዓት ይዝ መልካም ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡ የተማሩት በትምህርታቸው ደጃ አይመደቡ ማለቴም አይደም፡፡ ዛሬ እንደሚያውቁት ከለብ ለ ዩኒቨርሲቲዎች  በገንዘብ የዶክትሬት ዲግሪ እንደሚገዛ ይስቱታል ብዬ አልጠራጠርም፡፡ ነገር ግን ይህ ባለ ‹‹ዶክትሬቶቹን›› ለመመደብ ያበቃቸዋል ወይ ነው ጥያቄው?

  በአሜሪካ የመጀመያው ወጣት መሪ የ43 ዓመቱ ጎልማሳ ጆን ኤፍ ኬዲ ነበሩ፡፡ የእሳቸው አማካሪዎቻቸው በዕሜያቸው የበሰሉ በሥራቸው ተከብረውና ገርን በማገልል የተመሰከረላቸው በኩራዝ ተፈልገው ነበር ለአማካነት የሚፈለጉት፡፡ ባለፉት አርባ ዓመታ የተፈጠረው የካድሬ ውዥንብር አሁንም አቀቀንም፡፡ ይህ በአስቸኳይ በስዎ አገር ወዳድነት መስመር መያዝና አገራችን በማያጠራጥር ሁኔታ ወደፊት መገስገስ አለባት፡፡ እስከ ዛሬ ስንናንቀላፋ ከነበረው የቀሰቀሱን ይመስላልና ይበርቱበት፡፡                      እገር ወዳድነትዎን በንንግርዎና በአጀማመርዎ ሳይተዋል እያሳዩም ነው ይበርቱ፡፡ በዘርይማኖት መለያየት ለሌሎች ሲሳይ ለመሆን ካልሆነ በስተቀር ለወገን ጠቃሚ ስላልሆነ፣ ሕዝቡን በዚህ መንገድ ለመለየት የሚሞሩትን ሥፍራ አይስጧቸው፡፡ በቴክኖሎጂና በኢንዱስትሪ የምታብብ እንጂ በዘር የተከፋፈለ አገር ከለማኝነት አትወጣም፡፡ እነዚያ ሊለያዩን ሚሹ ተላላኪዎች ይህንን እንዲገነዘቡ ቢደረግ መልካም ይሆናል፡፡

  ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፣ እርግጠኛ ነኝ በየመንገዱ ሕፃን አዝላ ለልጄ ትምህርት ሳይሆን አንድ ቁራሽ ገዝቼ የማበላበትን ስጡኝ ብላ የምትለምነዋን ወጣት እንዳዩ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ለበርካታ ዓመታት ለአገሩ ሌት ከቀን ለፍቶ ያገለገለ ከሥራው ወጥቶ የሚበላውን አጥቶለት ጉርሱን እንደሚለምን አላዩም ብዬ አላስብም፡፡ ይህ ሁሉ ችግር ባለአገር የክልል ሹማምንት አጉል እሽቅድምድምና የቋንቋ ፉክክር ምን የሚሉት አባ ነው? ይህንን ተመልክተው ለዚህ መፍቴ ለመስጠት የሚችሉ ባለያዎችን ቢያሰባስቡ ኢትዮጵያን ይለወጧታል ብዬ ከልቤ ምናለሁ፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያያን ለዘለዓለም ያኑርልን ይዎታል፡፡

  ‹‹If we open a quarrel between the present and the past, we shall be in danger of losing the future›› (JFK) ይህ ፕሬዚዳንት ኬኔዲ ያለፈውን የዛሬውንና የነውን ለማስታረቅ የተናገሩት ምሳሌያዊ ቀራረብ ነበር፡፡ በመቀጠልም ካቶሊክ ስለሆንክ አትመረጥም የሚል አድማ ስለተነሳባቸው ቀጥሎ ያለውን ተናገሩ፣ ‹‹I do not speak for my church on public matters, and the church does not dpeak for me››. በግሌ የምረዳው ለኦሮሞማራ ለትግሬ ለወላይታ፣ ለአፋር ወይም ለሌላው ኅብረተሰብ ብቻ እንዳልቆሙ ነው፡፡ ታላቅ እንሆናለን ብለው በልም ሩጫ እንደ ተቀጠፉት አዶልፍ ትለርና ዱቼ ሞሎኒም ለግል ዝና የሚከንፉ አይመስለኝም፡፡ እምነትዎና አካሄድዎ ለኢትዮጵያ ንድነት ይመስለኛል፡፡ ይህ ከሆነ ጆሮዎን ጣል ዓይንዎን ከፈት ድርገው በቀና ከተጓ የዋሁ ደጉና እምብዛም ለክፋት ሰፊ ልብ የሌለው የአዎ ሕዝብ ከጎንዎ ይቆማልና ይበርቱ፡፡

  ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊው ግለ ሕይወታቸውንና የጉዞ ታሪካቸውን የከተቡበት ‹‹ከባቹማ እስከ ቨርጂኒያ›› በሚል ርዕስ ለአንባቢያን ያቀረቡት መጽሐፍ ደራሲ ሲሆኑ፣ ጽሑፉ የእሳቸውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን በኢሜይል አድራሻቸው assefadefris@gmail.com ማግኘት ይቻላል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በዓለም ጂኦ ፖለቲካ መድረክ የኢትዮጵያ ተፈላጊነት

  የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በሦስት የአፍሪካ አገሮች...

  በአገር ጉዳይ አንዱ ባለቤት ሌላው ባይተዋር መሆኑ ይብቃ!

  ኢትዮጵያ የታፈረችና የተከበረች አፍሪካዊት አገር ናት፡፡ ለመላው የዓለም ጥቁር...

  ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2015 የሒሳብ ዓመት ተቀማጭ ገንዘቡን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ለማሳደግ እንደሚሠራ አስታወቀ

  በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት በተለያዩ ክንውኖቹ ከዕቅድ በላይ ውጤት ማስመዝገቡን...