Friday, August 19, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ለግንባታ ዘርፍ ዋስትና ማስያዣ ለመስጠት ፍላጎታቸው እየቀነሰ መሆኑን ተናገሩ

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  ‹‹የኮንትራክተሮች አፈጻጸም ኩባንያዎቹን ጥርጣሬ ውስጥ ከቷ ቸዋል›› የኢትዮጵያ ሥራ ተቋራጭ ማኅበር

  በርካታ የግንባታ ፕሮጀክቶች በጊዜያቸው እየተጠናቀቁ ባለመሆናቸው የሚደርስባቸው ኪሳራ በመጨመሩ፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ለግንባታ ዘርፍ ዋስትና ማስያዣ (Guarantee Bond) ለመስጠት ያላቸው ፍላጎት መቀነሱ ተገለጸ።

  በአሁኑ ወቅት በርካታ የግንባታ ተቋራጮች የዋጋ ንረትንና ሌሎች ምክንያቶችን በማቅረብ ፕሮጀክቶቻቸውን በጊዜው እየፈጸሙ ባለመሆናቸው፣ በዋስትና ሰጪዎች በኩል ፍላጎት እየቀነሰ መሆኑን የናይል ኢንሹራንስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ንጉሥ አንተነህ ገልጸዋል።

  የግንባታ ዘርፍ ከፍተኛ ገንዘብ ፈሰስ የሚደረግበት በመሆኑ ለኢንሹራንስ ኩባንያዎችም የጋት መጠኑ በዚያው ልክ ከፍተኛ መሆኑን የሚገልጹት አቶ ንጉሥ፣ አደጋውን ለመቀነስ የዋስትና ማስያዣ ለመስጠት የሚወጡ መፈርቶችም እየበዙ እንደሆኑ ተናግረዋል።

  በጊዜያቸው ያልተጠናቀቁ በርካታ ፕሮጀክቶች ኮንትራታቸው እየተቋረጠ መሆኑን የሚገልጹት የኒያላ ኢንሹራንስ ዋና ራ አስፈሚ አቶ ያሬድ ሞላ ይህም ዘርፉ ላይ የሚኖረውን ተዓማኒነት ያሳጣዋል ይላሉ።

  በየጊዜው በግንባታ ዘርፉ ላይ በሚያጋጥሙት ችግሮች ዋስትና ሰጪ ለሆኑት ኢንሹራንስ ኩባንያዎች በየመቱ የሚሰጡትን የካሳ ክፍያ መጠን እንደ ጨመረው ተናግረዋል። በተለይም ለሞተርና ለእሳት አደጋ ዋስትናዎች ከተሰጠው የካሳ ክፍያ ቀጥሎ የግንባታ ዘርፍ ከፍተኛ ካሳ የተከፈለበት እንደሆነም አክለዋል።

  በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩ አካላትም በርካታ ፕሮጀክቶች በጊዜያቸው እየተፈጸሙ አለመሆኑን ይስማማሉ። የለማየሁ ከተማ ጠቅላላ ራ ተቋራጭ ባለቤትና ዋና ራ አስኪያጅ አቶ ለማየሁ ከተማ ኮንትራክተሮች የዋጋ መናርና የግብዓት አቅርቦቶች ፕሮጀክቶቻቸውን በጊዜው እንዳይፈጽሙ የሚያደርጉበት ሁኔታ በየመቱ እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል። ይህም ኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሚሰጡት የዋስትና ማስያዣን በቀላሉ ለማግኘት ከባድ እንዳደረገው አስረድተዋል

  ምንም እንኳን የዋጋ ንረትና የግብዓት አቅርቦት ከፍተኛ ችግር ቢሆ የግንባታ ራ ተቋራጮችም የጀመሯቸውን ፕሮጀክቶች ሳይፈሙ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን መጀመራቸው ኪሳራ ውስጥ እንዲገቡ እያደረጋቸው እንደሚገኝ አክለዋል።

  የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ራ ተቋራጮች ማበር ፕሬዳንት ግርማ ይለ ያም (ኢንነር) በበኩላቸው የግንባታ ዘርፉ የኮሮና ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ በከፍተኛ ፈተና ውስጥ እያለፈ መሆኑን ይገልጻሉ። በርካታ ራተኞችን የሚያሳትፈው ዘርፉ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የደረሰበት ኪሳራ በተለይ በመንግት በኩል ግምት ውስጥ ያልገባ ነው ብለዋል

  የሲሚንቶ፣ የብረትና የማጠናቀቂያ ቃዎች ዋጋ በየጊዜው መጨመር ለፕሮጀክቶች መጓተት ምክንያት ቢሆንም የተከሰተውን የዋጋ ንረት ከግምት ውስጥ ባለማስገባት በተለይ የመንግት ፕሮጀክቶች ውል ማቋረጥ ውስጥ መግባታቸው ትክክለኛ ርምጃ አለመሆኑን ግርማ (ኢንነር) ተናግረዋል።

  የፕሮጀክቶች መቋረጥና መጓተት በተለይ ኮንትራክተሩ የአፈጻጸም ብቃቱ ጥርጣሬ ውስጥ እንዲገባ በኢንሹራንስ ኩባንያዎች ዘንድም የሚፈልገውን ዋስትና እንዳያገኝ ያደርገዋል ብለዋል። በተለይ በግል ኮንትራክተሮች በተያዙ የመንግት ፕሮጀክቶች በኩል የሚወሰደው ውል የማቋረጥ ርምጃ እንዲስተካከል ለመንግት ጥያቄ ማቅረባቸውን በቅርብ ጊዜ ውስጥ መፍት ያገኛል ብለው እንደሚጠብቁ ገልጸዋል።

  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -spot_img

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች