Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊበቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ የልህቀት ማዕከላት ሊገነቡ ነው

  በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ የልህቀት ማዕከላት ሊገነቡ ነው

  ቀን:

  በኢትዮጵያ ከሚገኙት የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ በሰባ የልህቀት ማዕከላት እንደሚገነቡ፣ራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ።

  ማዕከላቱ የለም ባንክ በኢትዮጵያ፣ ያና ታንዛኒያ የሚተገረው የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ትስስር ፕሮጀክት (East Africa Skills for Transformation and Regional Integration Project-EASTRIP) አካል መሆኑን፣ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አበራ አባተ ለሪፖርተር ገልዋል።

  ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በመተግበር ላይ የሚገኘው ይህ ፕሮጀክት፣ በ16 የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ ለሚገነቡ የልህቀት ማዕከላት ድጋፍ ያደርጋል።

  በኢትዮጵያ ውስጥም ሰባት የልህቀት ማዕከላት የሚገነቡ ሲሆን፣ ማዕከላቱ ከሚገነቡባቸው ኮሌጆች መካከል ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ የሆለታ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና  ኮሌጅ፣ እንዲሁም የኮምቦልቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እንደሚገኙበት አቶ አበራ ገልጸዋል።

  ለመገንባት በዕቅድ ከተያዙት ሰባት የልህቀት ማዕከላት ውስጥ የስድስቱ  ማዕከላት  የዲዛይን ሥራ ተጠናቆ ግንባታውን የሚያከናውኑ አካላትን ለመለየት የሚያስችል የጨረታ ሒደት ላይ ይገኛልም ብለዋል፡፡ ሌላው ማዕከል በቢሾፍቱ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ውስጥ የሚገነባ ሲሆን፣ የግንባታ ከመሬት ጋር በተያያዘ ምክንያት መጓተቱን አብራርተዋል።

  ከሰባቱ ማዕከላት ውስጥ በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅና ኮምቦልቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ውስጥ የሚገነቡት ማዕከላት ትኩረት የሚያደርጉት ትራንስፖርትና መረተ ልማት ላይ ሲሆን በኃይል ላይ የሚያተኩረው ደግሞ በጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሚገነባው ማዕከል መሆኑን አቶ አበራ ገልዋል። ፌደራል ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ፣ በሐዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅና ሆለታ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ ውስጥ የሚገነቡት ማዕከላት ደግሞ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ትኩረት የሚሰጡ ናቸው ብለዋል።

  የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ትስስር ፕሮጀክት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ፕሮግራሞች ተደራሽነትን ማሳደግ፣ ጥራትን ማሻሻልና ቀጣናዊ ትስስርን ማሳለጥ ዓላማው አድርጎ የሚሠራ ሲሆን፣ የሚገነቡት የልህቀት ማዕከላትም በተለይ በኮሌጆቹና በኢንዱስትሪዎች መካከል ያለውን ትስስር የሚያጠናክሩ እንደሚሆኑ አቶ አበራ ገልጸዋል።

  ከዓለም ባንክ በተገኝ 300 ሚሊዮን ዶላር በጀት ተግባራዊ የሚደረገው ፕሮጀክቱ 70 በመቶ የሚሆነው በጀቱ በኢትዮጵያ፣ኬንያናታንዛንያ ውስጥ በሚገኙ 16 የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ ለሚገነቡ የልህቀት ማዕከላት የሚውል ነው

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...