Monday, August 8, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -

  ወደ ኮሌጅነት ያደገው የምድር ጦር ኦርኬስትራ

  የአዲስ አበባ 13ኛው ከተማ አቀፍ የኪነ ጥበብ ፌስቲቫል ‹‹በሥነ ጥበባት ኅብራዊ መልክ የተዋበች ኢትዮጵያ›› በሚል መሪ ቃል ከግንቦት 5 እስከ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በግዮን ሆቴል ቅጥር ግቢ ተካሂዷል፡፡ የተለያዩ የኪነ ጥበብ ሥራዎችና ዓውደ ርዕይ የቀረበበትም ነው፡፡ ለሰላም፣ ማኅበረሰብን ለመቅረፅ፣ ፍቅርን ለማስረፅና ሥነ ምግባርን ለመገንባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለማበርከት በተዘጋጀው ፌስቲቫል የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት፣ የአገር መከላከያ ኦርኬስትራ ቡድን፣ መረዋ ኳየርና የኢትዮጵያ ሰርከስ ማኅበር ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡ የሀገር ፍቅር ቴአትር፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር፣ ከየክፍላተ ከተማ የተውጣጡ የሙዚቃ ቡድኖችና የአገር መከላከያ የሙዚቃ ኮሌጅ በዓውደ ርዕይ ከተሳተፉት መካከል ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከል የቀድሞው የምድር ጦር ኦርኬስትራ ለኢንዱስትሪው ጉልህ ሚና ካላቸው ተቋማት ይጠቀሳል፡፡ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክም ብዙና አይረሴ አርቲስቶችን ካፈሩት ውስጥ ይመደባል፡፡ ሠራዊቱ ዳር ድንበሩን በትጋት እንዲጠብቅ፣ እንግዶችን በመቀበል ሥነ ሥርዓትና በሌሎችም ተግባሮች ጉልህ ሚና እንደነበረው ይነገራል፡፡ የአገር መከላከያ የሙዚቃ ኮሌጅ በቀድሞ ተግባሩና አሠራሩ ብዙ የሚነገርለትና የሚዘከርለት ተቋም ቢሆንም፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ የነበረውን ዝና አጥቷል የሚሉም አይታጡም፡፡ አሁን ላይ የአገር መከላከያ ሙዚቃ ኮሌጅ ከ300 በላይ የሙዚቃ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡ ተቋሙ የነበረውን ስምና ዝና ለመመለስ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተ የኮሌጁን መምህር ሻምበል ዮሴፍ ይርሳውን ሔለን ተስፋዬ አነጋግራቸዋለች፡፡

  ሪፖርተር፡- የመከላከያ ሙዚቃ ኮሌጅ መቼ ተመሠረተ?

  ሻምበል ዮሴፍ፡- የቀድሞ ስሙ የምድር ጦር የሙዚቃ ቡድን የሚል ነበር፡፡ የተመሠረተውም በ1935 ዓ.ም. ነው፡፡ ባለማቋረጥ እስካሁን የዘለቀ ቡድን ነው፡፡ በማርሽ ባንድ፣ በኦርኬስትራ፣ በቲያትር ክፍልና በሙዚቃ ትምህርት ቤት እየሠራ ይገኛል፡፡ ዘንድሮ ደግሞ ከሁሉም የጦር ሠራዊት የሙዚቃ ክፍሎችን በማሰባሰብ ኮሌጅ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በጦር ሠራዊት ክፍሉ ውስጥ ሙዚቃን ከሁሉም ለየት የሚያደርገው በሙዚቃ መቀዛቀዝ ሒደት ውስጥ እንኳን ሳይቋረጥ እስካሁን መቀጠሉ ነው፡፡ ትውልድና ዘመንን ወደ ነበረበት ከፍታ ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እያደረግን እንገኛለን፡፡ ለዚህም ትምህርት ቤት የነበረውን ወደ ኮሌጅ ማሳደግ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ የመከላከያ ሠራዊቱን ከማገልግል በተጨማሪ አገር አቀፍ የሙዚቃ ትምህርት መስጠት ጀምረናል፡፡ ከዚህ ቀደም ብዙ ሙዚቀኞች የሚመጡበት የጦር ሠራዊት ክፍለ ጦር እንደመሆኑ፣ ከማኅበረሰቡ ተቀብለን በርካታ ሙዚቀኞችን ለኢንዱስትሪው ለማበርከት እየሠራን ነው፡፡

  ሪፖርተር፡- የአገር ዳር ድንበር የሚጠብቁ ወታደሮችን በማበረታታትና ለፕሮግራሞች ድምቀት በመፍጠር የሙዚቃ ኮሌጁ ግንባር ቀደም ነው፡፡ አሁን ባለው የኢትዮጵያ የሰላም ሁኔታ አስተዋጽኦው እንዴት ይገለጻል?

  ሻምበል ዮሴፍ፡- ሠራዊቱን በሞራል በማነፅ፣ ለግዳጅ አፈጻጸሙ ብቁ ሥነ ልቦና እንዲኖረው በማድረግ ብዙ ሚና ተጫውቷል፡፡ በሠራዊት ምልመላ፣ የሽኝነት ወቅትና በምርቃታቸው ጊዜ በመገኘት በርካታ የቅስቀሳ ሥራዎች ሠርቷል፡፡ ትምህርት ቤቱም በሠራዊት ቅስቀሳ የሚሳተፉትን ሙያተኞች በማሠልጠን ለአገር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ የአገር ሰላምን ለማስጠበቅና ሰላሙ ዘላቂነት እንዲኖረው ሠራዊቱን ከማነሳሳት ጀምሮ ከፍተኛ ሥራን ይሠራል፡፡  

  ሪፖርተር፡- በቁጥር ምን ያህል አባላት አላችሁ? ኮሌጁ ከዚህ በፊት ያፈራቸው ሙዚቀኞችስ?

  ሻምበል ዮሴፍ፡- የመከላከያ ኦርኬስትራ ባንድ ቁጥራቸው ከ40 በላይ ናቸው፡፡ በትምህርት ክፍሉ ከ25 በላይ የሙዚቃ መምህራን አሉ፡፡ በአጠቃላይ 400 የሚሆኑ የሙዚቃ ተማሪዎች እየሠለጠኑ ይገኛሉ፡፡ ኮሌጁ ከ1985 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ መልክ ተቋቁሞ መሥራት ከጀመረ በኋላ 999 ሙዚቀኞችን አሠልጥኗል፡፡ አሁን ደግሞ 100 የሲዳማ ክልል ፖሊስ ማርሽ ባንድ ተማሪዎችን እያሠለጠነ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም 24 የመከላከያ ሙዚቃ ተማሪዎችን አንድ ላይ እያስተማረ ነው፡፡ ቡድኑ ካፈራቸው ዕውቅ ሰዎች መካከል አርቲስት ታምራት ሞላ፣ ጥላዬ ጨዋቃ፣ አምሃ ተወዳጅ፣ ሻለቃ ሾጌን ጨምሮ እንግሊዝ አገር ተምረው የመጡ የሙዚቃ ኮምፖዘሮች ይጠቅሳሉ፡፡   

  ሪፖርተር፡- አሁን ላይ የመቀዛቀዙ ምክንያት ምንድነው?

  ሻምበል ዮሴፍ፡- ይሄ የሁላችንም ጥያቄ ነው፡፡ እኛ በአሁኑ ጊዜ ከዘመኑ ጋር ለማጣጣምና የሚተኩ ባለሙያዎችን ለማፍራት ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እየሠራን እንገኛለን፡፡ ከዚህ ቀደም እንደተናገርኩት ከትምህርት ቤት ወደ ኮሌጅነት የማሳደጉ ሒደት አንዱ ምክንያት ሠራዊቱን ከማነቃቃት በተጨማሪ ለሙዚቃ ኢንዱስትሪው አስተዋጽኦ ለማበርከት ነው፡፡ ኮሌጁ በለውጥ ሒደት ላይ ነው፡፡ ከዚህ በኋላም ብዙ አዳዲስ ነገሮች ይኖሩታል ብለን እናምናለን፡፡  

  ሪፖርተር፡- የመከላከያ የሙዚቃ ኮሌጅ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ በርካታ ሙዚቀኞችን እንዳፈራ ገልጸውልናል፡፡ ይህንን ታሪካዊ የሙዚቃ ቡድን ለአሁኑ ትውልድ ከማሳወቅ አንፃር ኮሌጁ ምን እየሠራ ይገኛል?

  ሻምበል ዮሴፍ፡- ወጣቱ ትውልድ የመከላከያ ሙዚቃ ኮሌጅን ታሪክ እንዲረዳና ምን ያህል ሙያተኞችን እንዳፈራ በተለያዩ አጋጣሚዎች እናሳውቃለን፡፡ የወታደራዊ ክፍል ሙዚቀኞች በሥራዎቻቸው ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለወጣቶች ያስረዳሉ፡፡

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች ለማግኘት

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2015 የሒሳብ ዓመት ተቀማጭ ገንዘቡን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ለማሳደግ እንደሚሠራ አስታወቀ

  በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት በተለያዩ ክንውኖቹ ከዕቅድ በላይ ውጤት ማስመዝገቡን...

  በአገር ጉዳይ አንዱ ባለቤት ሌላው ባይተዋር መሆኑ ይብቃ!

  ኢትዮጵያ የታፈረችና የተከበረች አፍሪካዊት አገር ናት፡፡ ለመላው የዓለም ጥቁር...

  የዩኒቨርሲቲ መምህራን ከደመወዝ ጭማሪና ከዕርከን ዕድገት ጋር በተያያዘ መንግሥትን አስጠነቀቁ

  ‹‹የደመወዝ ጉዳይ የትምህርት ሚኒስቴር ብቻ ሳይሆን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንም...

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  የውጭ አገር ሕክምና የሚያስፈልጋቸውን እንግልት ለመቀነስ

  በኢትዮጵያ የሕክምና አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ ችግር እንዳለ ይታመናል፡፡ በተለይም በሕክምና ስህተት ሕሙማን ለሞት ሲጋለጡ አልያም ደግሞ ለሌላ ስቃይ ሲዳረጉም ይታያል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በዝቅተኛ...

  አሠሪና ሠራተኛ የሚገናኙበት ዓውደ ርዕይ

  በአዲስ አበባ ከተማ 23 ሚሊዮን ወጣቶች እንደሚኖሩ ከዓመት በፊት ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ያወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡ ከዚህ ውስጥ መሥራት የሚችሉ ወይም ዕድሜያቸው ለሥራ የደረሱ 75...

  የጎዳና ሕይወትን ለመከላከል የአንበሳውን ድርሻ መያዝ ያለበት ማነው?

  ማስተር ኤርሚያስ ገሠሠ የጳጉሜን አምስት ግብረ ሠናይ ድርጅት መሥራች ሥራ አስኪያጅና የማርሻል አርት አሠልጣኝ ናቸው፡፡ የግብረ ሠናይ ድርጅታቸውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ታደሰ ገብረማርያም አነጋግሯቸዋል፡፡ ሪፖርተር፡- የጳጉሜ...